የሩስያ ሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) በዩክሬን ሰሜናዊ ምስራቅ ካርኪቭ ግዛት ዛሬ አርብ ባደረሰው ጥቃት አንድ አውቶብስ በመመታቱ በከባድ ሁኔታ ውስጥ የሚገኝን አንድ ሰው ጨምሮ 6 ሠራተኞች መቁሰላቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ተናግረዋል፡፡
ሀገረ ገዥው ኦሌህ ሲኒዬኹቦቭ እንደተናገሩት ድርጊቱ የተፈፀመው ሩሲያ ባላፈው ግንቦት በከፈተችው የጦር ግንባር በኩል ከሀሊቦክ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው የደርሃቺ ተፈናቃዮች መጠለያ ከተማ አቅራቢያ ነው።
የዩክሬን ጦር፣ የሩስያ ጦር በድንበሩ አካባቢ 10 ኪሜ በመዘልቅ ሊያደርግ የነበረውን ግስጋሴ እንዲያቆም አድርጎታል፡፡
ሩሲያ እኤአ በየካቲት 2022 ሙሉ የዩክሬን ወረራን ከጀመረች ወዲህ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል፡፡
መድረክ / ፎረም