በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ከሩሲያ ጋር በተደረገ ታሪካዊ  የእስረኛ  ልውውጥ አሜሪካዊያን እስረኞች ማስለቀቋን አስታወቀች፡፡  


 እስረኞችን ይዘው ከሩሲያ እንደመጡ የታመኑ አውሮፕላኖቹ ቱርክ አንካራ አየር ማረፊያ ሲደርሱ፣ ሐምሌ 25 ቀን 2016 ዓ.ም.
እስረኞችን ይዘው ከሩሲያ እንደመጡ የታመኑ አውሮፕላኖቹ ቱርክ አንካራ አየር ማረፊያ ሲደርሱ፣ ሐምሌ 25 ቀን 2016 ዓ.ም.

ዩናይትድ ስቴትስ ከሩሲያ ጋር ታሪካዊ የእስረኛ ልውውጥ አድርጋ እስረኞች ማስለቀቋን ዛሬ ሐሙስ አረጋግጣለች፡፡ በእስረኛ ልውውጡ አሜሪካዊያኑን ጋዜጠኞች ኢቫን ጌርሽኮቪች እና አልሱ ኩርማሼቫ እንዲሁም የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ማሪን ኮር ሠራዊት መኮንኑ ፖል ዌላን እና የአሜሪካ ቋሚ ነዋሪ ቪላዲሚር ካራ ሙርዛ ተለቀቅዋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ በጠቅላላው አስራ ስድስት ሰዎችን ያስለቀቀች ሲሆን ከመካከላቸው ሩስያ ያሰረቻቸው አምስት ጀርመናዊያን እንዲሁም ሰባት የሩሲያ ዜጎች እንዳሉባቸው ተመልክቷል፡፡ በልዋጩ ዩናይትድ ስቴትስ፡ ጀርመን፡ ፖላንድ፡ ኖርዌይ እና ስሎቬኒያ ውስጥ ታስረው የነበሩ ሩስያዊያን ተለቅቀዋል፡፡

ይህ በዩናይትድ ስቴትስ እና በሩሲያ መካከል ከቀዝቃዛው ጦርነት ወዲህ ትልቁ የእስረኞች ልውውጥ መሆኑ ታውቋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የብሔራዊ ጸጥታ አማካሪ ጄክ ሰለቫን ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል “ እጅግ ብዙ ወራት በፈጀ ውስብስብ እና ብርቱ ድርድር የተገኘ ውጤት “ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የእስረኛ ልውውጡ ለመጀመሪያ ጊዜ በርካታ ሀገሮች እና ሸሪኮች በትብብር ያለአግባብ ታስረው የቆዩ ሰዎች ለማስለቀቅ የቻሉበት መሆኑንም ጄክ ሰለቫን አውስተዋል፡፡

በእስረኛ ልውውጡ ከተለቀቁት አሜሪካዊያን መካከል አንዱ ከሁሉም ለረዘመ ጊዜ ሩሲያ ውስጥ ታስረው የቆዩት ፖል ዌላን ናቸው፡፡ ፖል እ አ እ በ2018 ሞስኮ ውስጥ ከተያዙ በኋላ በ2020 በስለላ ወንጀል በቀረበባቸው ክስ የ16 ዓመት እስራት የተፈረደባቸው ናቸው፡፡ እርሳቸውም የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥትም ክሱን አስተባብለዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG