በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ናይጄሪያ ውስጥ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ 19 ሰዎች ተገደሉ


ምስሉ የቦርኖ ግዛት የሚገኝበት የናይጄሪያ ካርታ ያሳያል
ምስሉ የቦርኖ ግዛት የሚገኝበት የናይጄሪያ ካርታ ያሳያል

በናይጄሪያ ቦርኖ ክፍለ ግዛት ሰው በሚበዛበት የሻይ ቤት ውስጥ ቦምብ ፈንድቶ 19 ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች ቢያንስ 20 ሰዎች መቁሰላቸውን የክፍለ ግዛቷ ባለስልጣናት አስታወቁ፡፡

ፍንዳታው የደረሰው ትላንት ረቡዕ ማታ ሲሆን በሀገሪቱ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ሁለተኛው የቦምብ ፍንዳታ መሆኑ ታውቋል፡፡

ከቦርኖ ክፍለ ግዛት ዋና ከተማ ከማይዱጉሪ ሃምሳ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ባለች መንደር የደረሰው ጥቃት የአጥፍቶ ጠፊ ድርጊት እንዳልነበረ ባለስልጣናቱ አመልክተዋል፡፡ ለጥቃቱ ኅላፊነት የወሰደ አካል የለም፡፡ ሆኖም ቦርኖ ክፍለ ግዛት ውስጥ ጂሃዳዊው ቦኮ ሀራም እና የምዕራብ አፍሪካ እስላማዊ መንግሥት የተባለው ቡድን በብዛት ይንቀሳቀሳሉ፡፡

ከጥቂት ሳምንታት በፊት ጉዎዛ በተባለ የቦርኖ ክፍለ ግዛት አካባቢ ሴት አጥፍቶ ጠፊዎች በተቀናጀ መንገድ ባደረሱዋቸው ጥቃቶች ሠላሳ ሁለት ሰዎች መግደላቸው ይታወሳል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG