የእሁዱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫን ተከትሎ በመላ ቬንዙዌላ ብጥብጡ እየጨመረ ሲሄድ መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው የካርተር ማእከል የቬኒዙዌላ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ “ዲሞክራሲያዊ ሊባል እንደማይችል” አስታውቋል።
የካርተር ማዕከል ፕሬዚዳንት ኒኮላስ ማዱሮ አሸናፊ በማድረግ ያበቃው አጨቃጫቂው ምርጫ “ዲሞክራሲያዊ ሊባል አይችልም” ብሏል።
በቀድሞው ፕሬዝዳንት ጂሚ ካርተር እና በሟች ባለቤታቸው ሮዛሊን የተመሰረተው መንግሥታዊ ያልሆነው ድርጅት 17 የምርጫ ባለሙያዎችን ቡድን ወደ ደቡብ አሜሪካዪቱ ሀገር በማሰማራት ምርጫውን ለመታዘብ መቻሉን ገልጿል።
ማዕከሉ ትላንት ማክሰኞ መገባደጃ ላይ በሰጠው መግለጫ ምርጫው “ዓለም አቀፍ የምርጫ ታማኝነት መስፈርቶችን አያሟላም” ብሏል።
ማዱሮ ይቆጣጠሩታል የተባለው የቬንዙዌላ ምርጫ ምክር ቤት ሰኞ ማለዳ ላይ እንዳስታወቀው ፕሬዚዳንቱ በምርጫው 51 በመቶ ድምጽ በማግኘታቸው 44 በመቶ ድምጽ ያገኙትን ተፎካካሪያቸው ኤድመንዶ ጎንዛሌዝን አሸንፈዋል ብሏል።
ድምጽ ሰጭዎች ከምርጫው በኋላ የሰጡት ድምጽ ጎንዛሌዝ በከፍተኛ ልዩነት ማሸነፋቸውን የሚያሳይ በመሆኑ የምክር ቤቱን ውጤት በእጅጉ እንደሚቃረን ተመልክቷል፡፡
የካርተር ማዕከል ምክር ቤቱ ከእያንዳንዱ የምርጫ ማዕከላት የተሰጡ የድምጽ መጠኖችን ያላካተተ በመሆኑ ውጤቱን ማረጋገጥ እንዳልቻለ ገልጿል፡፡
ማዕከሉ ጨምሮ እንዳስታወቀው የምርጫ ምክር ቤት እርምጃዎች የመራጮች ምዝገባ ችግሮች እና የተቃዋሚ ዘመቻ ጣልቃ ገብነትን ጨምሮ ለማዱሮ ግልፅ የሆነ አድልዎ ያሳያል ብሏል፡፡
በመላው ቬኒዙዌላ ምርጫውን ውጤት ተከትሎ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ወደ ሁከት ተቀይሮ በትንሹ 16 ሰዎች ተገድለዋል፡፡
መድረክ / ፎረም