በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በገዜ ጎፋ ወረዳ የመሬት መንሸራተት አደጋ ተጨማሪ የ12 ሟቾች አስከሬን መገኘቱ ተገለጸ


በመሬት መንሸራተት አደጋው ልጇን ያጣችው የ43 አመቷ እናት ዘሪቱ ዘካርያስ (REUTERS/Kumerra Gemechu TPX IMAGES OF THE DAY)
በመሬት መንሸራተት አደጋው ልጇን ያጣችው የ43 አመቷ እናት ዘሪቱ ዘካርያስ (REUTERS/Kumerra Gemechu TPX IMAGES OF THE DAY)

በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሞቱ ተጨማሪ የ12 ሰዎች አስከሬን መገኘቱን፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው ኃላፊ ወይዘሮ ሠናይት ሰሎሞን፣ ዛሬ ማክሰኞ በሰጡት መግለጫ፣ እስከ አሁን የተገኙ አስከሬኖች ጠቅላላ ቁጥር 243 መድረሱን አረጋግጠዋል፡፡

በአደጋው ቤተሰቦቻቸውን፣ ወዳጆቻቸውንና ዘመዶቻቸውን ያጡ የገዜ ጎፋ ወረዳ ነዋሪዎች፣ አሁንም በከፍተኛ ድንጋጤ እና ኀዘን ውስጥ መኾናቸውን ኃላፊዋ ገልጸዋል፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:07:02 0:00

የአሜሪካ ድምፅ ካነጋገራቸው ተጎጂዎች ውስጥ የኾኑ አዛውንት፣ “በመጦሪያ ዕድሜዬ ባለቤቴንና 15 የቅርብ ዘመዶቼን በአደጋው አጥቻለኹ፤ ብቻዬን ቀርቻለኹ፤” ሲሉ ያሉበትን ኹኔታ አስረድተዋል፡፡

የአደጋው ሰለባዎች የታሰቡበት የሦስት ቀናት ብሔራዊ ኀዘን ዐዋጁ፣ ትላንት ሰኞ ሲጠናቀቅ፣ በኹሉም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አካባቢዎች፣ አደባባይ በመውጣት በሻማ ማብራት ኀዘንን የመግለጽ ሥነ ሥርዓት ተከናውኗል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይመልከቱ፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG