የሰው ሰራሽ ልሕቀት በሰዎች የዕለት ተዕለት ኑሮ እያሳደረ ያለው ተጸዕኖ እየጎላ መምጣቱ የብዙዎችን ትኩረት የሚስብ የውይይት ርዕስ ቢያደርገውም፤ እስካሁን የዩናይትድ ስቴትስ መራጮችን ከሚያሳስቡ ዋና ዋና ጉዳዮች ተርታ አላሰለፈውም።
ሆኖም በፍጥነት በማደግ ላይ ያለው ይህ ቴክኖሎጂ በሚመራበት ፖሊሲ ዙሪያ ተፎካካሪው ፕሬዚዳንታዊ እጩዎች ያሏቸውን ፍጹም ለየቅል የሆኑ ራእዮች የሚያስተዋውቁበት የመጀመሪያው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ይሆናል ተብሏል።
መድረክ / ፎረም