በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰሜን ኮሪያው መሪ የሰውነታቸው ክብደት አስግቷል


የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን እና ሴት ልጃቸው ኪም ጁ ኤ በሰሜን ኮሪያ በሚገኘው የጋንግዶንግ ግሪን ሃውስ የመክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ ፣ በመጋቢት 7 ቀን 2024 ዓ.ም. የተለቀቀ ምስል
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን እና ሴት ልጃቸው ኪም ጁ ኤ በሰሜን ኮሪያ በሚገኘው የጋንግዶንግ ግሪን ሃውስ የመክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ ፣ በመጋቢት 7 ቀን 2024 ዓ.ም. የተለቀቀ ምስል

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን የሰውነታቸው ክብደት እንደገና በመጨመሩ ከውፍረት ጋር ለተያያዙ የደም ግፊት እና የስኳር በሽታ ለመሳሰሉ የጤና ችግሮች መዳረጋቸው ተዘገበ።

የደቡብ ኮሪያ ብሄራዊ መረጃ አገልግሎት የሰሜን ኮሪያ ባለስልጣናት የኪምን የጤና ጉድለቶች ለማከም በውጭ አገር አዳዲስ መድሃኒቶችን እያፈላለጉ እንደሆነ አስታውቋል።

የ40 አመቱ ኪም አለመጠን በመጠጣት እና በማጨስ ይታወቃሉ፡፡ የልብ ችግር ታሪክ ካለው ቤተሰብ የመጡ ሲሆን አባትና እና አያታቸው የሞቱት በልብ ህመም ነው፡፡

እ.ኤ.አ. በ 2021 ኪም አመጋገባቸውን በመቀየር ክብደታቸውን ለመቀነስ ችለው ነበር፡፡ በቅርብ ጊዜ የታዩ ምስሎች ግን የሰውነት ክብደታቸው ወደ ቦታው መመለሱን ሲያሳዩ ፣ አሁን 140 ኪሎግራም (308 ፓውንድ) እንደሆኑ ተዘግቧል፡፡

ኪም ለልብ ህመም ከፍተኛ ተጋላጭነት ካላቸው ሰዎች እንደሚመደቡ ሲነገር ከ30ዎቹ ዓመታት መግቢያ ጀምሮ የደም ግፊት እና የስኳር በሽታ ምልክቶች እንደታዩባቸው የህክምና ምንጮችን የጠቀሰው አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

ኪም ጆንግ ኡን እንደ መጠጥ፣ ማጨስ እና ጭንቀት ለመሳሰሉ የአኗኗር ችግሮች የተጋለጡ መሆናቸው ተዘግቧል፡፡

የኪም አቅምና ጤና ማጣት የኒውክለር ጦር መሳሪያ ባለቤት በሆነችው ሀገር እሳቸውን የሚተካ መሪ ባለመገለጹ በዓለም አቀፍ ደረጃ የጤናቸው ጉዳይ የቅርብ ክትትል አስከትሏል፡፡

ምንም እንኳ በይፋ ባይገለጽም ኪም የ10 ዓመቷ ሴት ልጃቸው ኪም ጁ ኤ የአባቷ አልጋ ወራሽ እንደምትሆን ጠቆም ማድረጋቸው ተነግሯል፡፡

ኪም ጁ ኤ እኤአ ከ2022 መገባደጃ ጀምሮ ከአባቷ ጋር በከፍተኛ ደረጃ በሚታወቁ ህዝባዊ እና ወታደራዊ ዝግጅቶች ላይ ተገኝታለች፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG