ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ፍጻሜ በኋላ፣ በዐማራ ክልል ከተቋቋሙት የራያ አላማጣ እና የራያ ባላ ወረዳዎች እንዲሁም የአላማጣ ከተማ፣ በቅርቡ ተከሰተ ባሉት የጸጥታ ችግር ምክንያት ተፈናቅለው በሰሜንና በደቡብ ወሎ ዞኖች ከተሞች እና የገጠር ቀበሌዎች እንደሚገኙ የገለጹ ነዋሪዎች፣ ወደ ቀዬአቸው መመለስ እንዳልቻሉ ገልጸው ፤ ቅሬታ አሰሙ።
ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የሰጡ ተፈናቃዮች፣ አሁን ባለው የኑሮ ውድነት እና እየከበደ በመጣው የክረምት ወቅት፣ በተፈናቃይነት በመጠለያ ካምፕም ኾነ ከቤተሰብ ጋራ ተዳብሎ መኖር አዳጋች እንደኾነባቸው አስታውቀዋል፡፡
በቅርቡ፣ በራያ አላማጣ አካባቢ ተቀስቅሷል የተባለውን የጸጥታ ችግር ተከትሎ ወደ ሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከ70ሺሕ ማለፉን፣ የራያ አላማጣ ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ አመልክተዋል።
የራያ ወሎ ዐማራ ማንነት እና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኀይሉ አበራ ደግሞ፣ ተፈናቃዮችን ወደ ቀዬአቸው ለመመለስ የተደረገው ሙከራ አለመሳካቱን ገልጸዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ይከታተሉ፡፡
መድረክ / ፎረም