በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ በዩክሬን ዶነስክ ግዛት ባደረሰችው ጥቃት አምስት ሰዎች ተደገሉ፤ 15 ቆሰሉ


ፋይል፤ እንደ አውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር ጁላይ 22 ቀን 2024 ዓ.ም. ሩሲያ ጥቃት ባደረሰችበት ዶነስክ ግዛት አካባቢ በሚገኝ መንደር ውስጥ አንዲት እናት የፈራረሰውን መንደር ቆመው ሲመለከቱ።
ፋይል፤ እንደ አውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር ጁላይ 22 ቀን 2024 ዓ.ም. ሩሲያ ጥቃት ባደረሰችበት ዶነስክ ግዛት አካባቢ በሚገኝ መንደር ውስጥ አንዲት እናት የፈራረሰውን መንደር ቆመው ሲመለከቱ።

ሩሲያ በዩክሬን ምስራቃዊ ክልል በምትገኘው ዶነስክ ግዛት ባደረሰችው ጥቃት አምስት ሲቪሎች ሲገደሉ፣ 15 ሰዎች መቁሰላቸውን የአካባቢው ባለሥልጣናት አስታወቁ።

የዶነስክ ገዥ ቫዲም ፊላሽኪን ዛሬ እሁድ ስለጥቃቱ ከተናገሩ በኋላ፣ ሌሎች የዩክሬን ባለሥልጣናት ሩሲያ በምስራቅ እና በደቡብ የዩክሬን አካባቢዎች ያደረሰችው ጥቃት ተጨማሪ ሲቪሎች ማቁሰሉን አስታውቀዋል።

ሞስኮ በዩክሬን ማዕከላዊ የኢንዱስትሪ አካባቢ እያካሄደች ላለችው ወራት የፈጀ የማጥቃት ርምጃ፣ ተጨማሪ ትርፍ እንዳገኘች አስታውቃለች።

ዛሬ እሁድ፣ የሞስኮ ጦር በምስራቃዊ ዩክሬን በምትገኘው ኒኮፖል ከተማ ላይ ያደረሰውን ጥቃት ተከትሎ፣ አንድ ሕጻን እና የ10 ዓመት አዳጊን ጨምሮ ስምንት ሰዎች መጎዳታቸውን እና ከእነዚኽም መካከል ስድስቱ ሆስፒታል ገብተው በመታከም ላይ እንደሚገኙ የአካባቢው አስተዳዳሪ ሰርሂ ሊሳክ አስታውቀዋል።

በተጨማሪም፣ በዩክሬን ደቡባዊ ኬርሰን ግዛት በሚገኝ መንደር ውስጥ በደረሰ ጥቃት አንድ የ10 እና ሁለት አዳጊዎችን ጨምሮ ስምንት ሰላማዊ ሰዎችን የሩሲያ ወታደሮች ማቁሰላቸውን፣ ሮማን ሚሮክኮ የተባሉ የአካባቢው ባለሥልጣን አስታውቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG