በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፓርላማው በመሬት መንሸራተት አደጋ ለሞቱ ወገኖች ብሔራዊ የኀዘን ቀን ዐዋጀ


የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በተከሠተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች፣ የሦስት ቀናት ብሔራዊ ኀዘን ዐውጇል፡፡

በምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ስም፣ ዛሬ ዐርብ የወጣው መግለጫ፣ ከነገ ሐምሌ 20 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ለሦስት ቀናት፣ በአደጋው ሕይወታቸውን ያጡ ዜጎችን በማሰብ ብሔራዊ የኀዘን ቀን ኾኖ እንዲታወጅና የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ መወሰኑን አስታውቋል፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:06:29 0:00

በተያያዘ ዜና፣ በካፋ እና በቤንች ሸኮ ዞኖች፣ ከትላንት በስቲያ ረቡዕ ሌሊት በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ፣ ሁለት ሕፃናትን ጨምሮ ስድስት ሰዎች መሞታቸውን፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽንና ኮምዩኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል፡፡

በደቡባዊ ኢትዮጵያ፣ ከረቡዕ ሌሊቱ አደጋ ጋራ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት የቀጠፉ ሦስት የመሬት መንሸራተት አደጋዎች በአንድ ሳምንት ውስጥ መከሠታቸውን አስመልክቶ የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የመሬት ጥናት ባለሞያ፣ “አደጋዎቹ ከመሬት አጠቃቀምና ከአየር ኹኔታ ጋራ የተያያዙ ናቸው፤” ሲሉ አስረድተዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ይከታተሉ፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG