በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ የምጣኔ ሃብት የ2 ነጥብ 8 በመቶ እድገት ማስመዝገቡ ተገለጠ


ፋይል - የአማዞን ሰራተኞች በደቡብ ጌት ካሊፍ ውስጥ በሚገኘው የአማዞን መጋዘን ጣቢያ በስራ ላይ ሐምሌ 9 ቀን 2016 ዓ.ም. (AP Photo/Richard Vogel, File) )
ፋይል - የአማዞን ሰራተኞች በደቡብ ጌት ካሊፍ ውስጥ በሚገኘው የአማዞን መጋዘን ጣቢያ በስራ ላይ ሐምሌ 9 ቀን 2016 ዓ.ም. (AP Photo/Richard Vogel, File) )

ያልተቋረጠ የከፍተኛ ወለድ ተመን ጫና ያልተለየው የዩናይትድ ስቴትስ የምጣኔ ሃብት፤ ባለፈው ሩብ ዓመት በአመታዊ የእድገት ፍጥነት ሲሰላ ጠንካራ የሚሰኝ የ2 ነጥብ 8 በመቶ ጭማሬ ማሳየቱን ተዘገበ። የሸማቾች የመግዛት ፍላጎት እና የንግድ እንቅስቃሴዎች መጎልበት ለተመዘገበው እድገት ዓይነተኞቹ ምክኒያቶች መሆናቸውም ተመልክቷል።

ከጥር እስከ መጋቢት ወር በነበረው የ2024 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የ 1 ነጥብ 4 በመቶ የእድገት ፍጥነት ያስመዘገበው አጠቃላይ የሃገር ውስጥ ምርት ከሚያዝያ እስከ ሰኔ ወር ድረስ በነበረው ተከታዩ የሩብ ዓመት እጥፍ በሆነ ፍጥነት እድገት ማሳየቱ ተጠቁሟል።

የምጣኔ ሃብት ባለሞያዎች የ1 ነጥብ 9 በመቶ ደከም ያለ አመታዊ እድገት ጠብቀው እንደነበር፣ ሆኖም ከዚያ በእጅጉ በተሻለ ፍጥነት ማደጉ እና የዋጋ ግሽበትን አስመልክቶም ምንም እንኳን አሁንም የፌዴራል ገንዘብ ሚንስቴር ከ2 በመቶ ያልበለጠ የዋጋ ንረት ጣሪያ እንዳያልፍ ከያዘው ግብ ባይደርስም፤ ቀደም ሲል ታይቶ የነበረው የዋጋ ንረት ማሽቆልቆል ዝንባሌ ግን አሁንም መቀጠሉን የሃገር ውስጥ ምርት ሪፖርቱ አሳይቷል።

በሌላ በኩል የዩናይትድ ስቴትስ ምጣኔ ሃብት የገንዘብ ሚንስቴር የሚደነግገው ከፍተኛ የወለድ ተመን፤ ኢኮኖሚውን ወደ ውድቀት ሳያመራ የዋጋ ግሽበቱን ለማርገብ በሚል የወሰደው እርምጃ እምብዛም ያልተለመደ የተባለውን ‘ዝግ ያለ የመረጋጋት’ አዝማሚያ አዲስ ይፋ የተደረጉት አሃዞች በሃገሪቱ ምጣኔ ሃብት ይዞታ ላይ የሚኖረውን ‘የመተማመን ከፍ ያደርጉት ይሆናል’ ተብሎም ተጠብቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG