በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብ ምሥራቅ እስያ አገራት ጉባኤ፣ ቻይና እና ጃፓን ይነጋገራሉ


ፋይል - በደቡብ ኮሪያ ቡሳን በተካሄደው 10ኛው የሶስትዮሽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ የደቡብ ኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፓርክ ጂን፣ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪን እና የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዮኮ ካሚካዋን ፣ ኅዳር 16 ቀን 2016 ዓ.ም.
ፋይል - በደቡብ ኮሪያ ቡሳን በተካሄደው 10ኛው የሶስትዮሽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ የደቡብ ኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፓርክ ጂን፣ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪን እና የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዮኮ ካሚካዋን ፣ ኅዳር 16 ቀን 2016 ዓ.ም.

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ እና የጃፓኑ አቻቸው ዮኮ ካሚካዋ በያዝነው ሳምንት በላኦሷ ዋና ከተማ ቪንቲያን ከሚካሄደው የደቡብ ምሥራቅ እስያ አገራት ማሕበር ጉባኤ - ‘አዥያን’ ትይዩ ተገናኝተው ይነጋገራሉ ተብሎ ተጠብቋል።

በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ የቻይናው ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማ ዣውሹ ቶኪዮ ላይ ከጃፓኑ አቻቸው ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል። ማ በቶኪዮው ቆይታቸው ቀጥሎም ከካሚካዋ ጋር ተገናኝተው መወያየታቸው ተዘግቧል።

ሁለቱ አገሮች እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2020 ወዲህ በጋራ ስትራተጂያዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሲነጋገሩ የአሁኑ የመጀመሪያቸው ነው። መንግሥታዊው የቻይና የዜና ወኪል ግሎባል ታይምስ “ሁለቱ ወገኖች በቻይና እና በጃፓን ግንኙነት ላይ ባተኮሩ ዋና ዋና ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች ላይ በቅን ልቦና ጥልቅ የሃሳብ ልውውጥ አድርገዋል” ሲል ዘግቧል።

የጃፓኑ ኪዮዶ የዜና አገልግሎት በበኩሉ የመንግስት ምንጮችን ጠቅሶ ከላኦሱ ጉባኤ አስቀድሞ ባስነበበው ዘገባ ቶኪዮ ዋንግ እና ካሚካዋ ከጉባኤው ትይዩ ሊነጋገሩ ስለሚችሉበት ሁኔታ እያሰበች ነው ብሏል። ይሁን እንጂ ይህን አስመልክቶ እስካሁን ከሁለቱም ወገኖች የተሰማ ማረጋገጫ የለም።

የሁለቱ አገሮች ግንኙነት በበርካታ ምክኒያቶች ሻክሮ የቆየ ሲሆን፤ ውይይታቸውም በቀላሉ መግባባት የማይችሉባቸውን እና የሚያከራክሩ ጉዳዮች ሊጨምር እንደሚችልም ተገምቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG