በደቡብ ሜጫ ወረዳ፣ “የሰላም ኮሚቴ አባል ኾናችኋል” በሚል በስፍራው በሚንቀሳቀሱ የፋኖ ታጣቂዎች መያዛቸው ከተገለጸው ከ13 በላይ ሰዎች ውስጥ፣ ቢያንስ አራቱ መገደላቸውን ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡
“ገርጨጭ” በተባለች የወረዳው ከተማ፣ “አራት ሰዎች ጭካኔ በተሞላበት መንገድ ተገድለዋል፤” ያለው የዐማራ ክልል መንግሥት፣ “ጽንፈኛ ኀይሎች” ሲል የጠራቸውን አካላት ተጠያቂ አድርጓል፡፡
ከወረዳው “አባላትን አልመለመልሁም” ያለው የዐማራ ክልል የሰላም ምክር ቤት በበኩሉ፣ ግድያውን አጥብቆ እንደሚያወግዝ ገልጿል፡፡
የአሜሪካ ድምፅ፣ ከፋኖ ታጣቂዎች በኩል አስተያየት ለማግኘት ያደረገው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያድምጡ
መድረክ / ፎረም