በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በገዜ ጎፋ ወረዳ የመሬት ናዳ የሟቾች ቁጥር 250 ደረሰ


በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በደረሰው የመሬት ናዳ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 250 መድረሱንና የነፍስ አድን ጥረቱ ተጠናክሮ መቀጠሉን፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታወቀ።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት እና አጋር ድርጅቶች፣ በአደጋው የተሰማቸውን ኀዘን ገልጸው ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:04:30 0:00

በወረዳው ያጋጠመው አሳሳቢ የተፈጥሮ አደጋ ያስከተለውን ሞት እና ጉዳት የሚመጣጠን የምግብ እና መሠረታዊ የሰብአዊ ድጋፎች፣ በተቀናጀ መልኩና በአፋጣኝ ሊቀርብ ይገባል፤ ሲል፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አሳስቧል፡፡

በተያያዘ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በቤንች ሸኮ ዞን ሰሜን ቤንች ወረዳ በደረሰ የመሬት ናዳ እና መሠንጠቅ፣ 208 ሰዎች ከቀዬቸው መፈናቀላቸው ተገልጿል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይድምጡ፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG