ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ከምርጫው ራሳቸውን ማግለላቸውን በተመለከተና “ወደፊት ስለሚሆነው” እንዲሁም “ለአሜሪካ ሕዝብ በመከወን ላይ ያሉትን ሥራ እንዴት እንደሚያጠናቅቁ” እና መሰል ጉዳዮችን በተመለከተ ዛሬ ማምሻውን ለሕዝቡ ንግግር እንደሚያደርጉ በ X ማኅበራዊ መድረካቸው ላይ አስታውቀዋል።
የንግግራቸውን ዝርዝር ይዘት በተመለከተ ዋሽንግተን ላይ በሪፖርተሮች የተጠየቁት ባይደን፣ “ጠብቃችሁ ተመልከቱ፣ አድምጡ” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
በኮሮና ቫይረስ በመያዛቸው ምክንያት በዴለዌር ግዛት በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ለአንድ ሳምንት የቆዩት ባይደን፣ ትላንት ማክሰኞ ወደ ዋይት ሃውስ ተመልሰዋል። ሐኪማቸው ዶ/ር ከቪን ኦ’ኮነር፣ ባይደን ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸውን ትላንት አስታውቀዋል።
ባይደን ንግግራቸውን የሚያደርጉት በዋሽንግተን አቆጣጠር ከምሽቱ 8 ሰዓት ወይም በኢትዮጵያ አቆጣጣር ከሌሊቱ 9 ሰዓት እንደሆነ ታውቋል።
መድረክ / ፎረም