በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእስራኤል ኃይሎች በጋዛ የምትገኘውን ካን ዩኒስ ከተማ ደበደቡ


የእስራኤል ጦር ተዋጊ ጄት ፡ ሐምሌ 17 ቀን 2016 ዓ.ም.
የእስራኤል ጦር ተዋጊ ጄት ፡ ሐምሌ 17 ቀን 2016 ዓ.ም.

የእስራኤል ኃይሎች በጋዛ የምትገኘውን የካን ዩኒስ ከተማ በምድር እና በአየር እንደደበደቡ፣ የሃገሪቱ ሠራዊት ዛሬ ረቡዕ አስታውቋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለስልጣናት ጉዳዩ እንዳሳሰባቸው ሲገልጹ፣ አንድ የተመድ የሰብዓዊ ድርጅት በበኩሉ ትላንት እንዳስታወቀው፣ እስራኤል ሕዝቡ ለቆ እንዲወጣ ማሳሰቧን ተከትሎ 150ሺሕ የሚሆኑ ነዋሪዎች ካን ዩኒስን ለቀው ወጥተዋል።

ነዋሪዎች ለቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ በተሰጠበትና፣ የእስራኤል ኃይሎች ጥቃት በፈጸሙበት መካከል የነበረው ጊዜ አጭር እንደነበር የተመድ ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ቃል አቀባይ የሆኑት ስቴፋን ዱጃሪክ ትላንት ለዜና ሰዎች አስታውቀዋል።

እያንዳንዱ የለቃችሁ ውጡ ማስጠንቀቂያ የሰዎችን ሕይወት የሚያመሳቅል መሆኑና አነስተኛ ወይም ምንም ዓይነት መሠረተ ልማት ወደሌለበት አካባቢ እንዲሄዱ እንደሚገደዱ ቃል አቀባዩ ጨምረው ተናግረዋል። መጠለያ፣ የጤና፣ የንጽህና አገልግሎት፣እንዲሁም የሕይወት አድን ሰብዓዊ ዕርዳታ በተወሰነ ደርጃ ብቻ ወደሚገኙባቸው አካባባዎች ለመሄድ እንደሚገደዱም አስታውቀዋል።

በደቡባዊዋ የጋዛ ከተማ ራፋ ላይ ጥቃት መሰንዘሩን እንዲሁም በመላ የጋዛ ሰርጥ ደግሞ በደርዘን የሚቆጠሩ የአየር ድብደባዎችን ማድረጉን የእስራኤል ሠራዊት ዛሬ ረቡዕ አስታውቋል።

በዛሬው ድብደባ የተገደሉ 55 ሰዎች አስከሬኖች ሆስፒታል መድረሳቸውንና ጦርነቱ ከጀመረ አንስቶ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 39ሺሕ 145 መድረሱን በጋዛ የሚገኘው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG