ዶናልድ ትራምፕ ከግድያ ሙከራ ከተረፉ ወዲህ የመጀመሪያ በሆነው የድጋፍ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ በመገኘት የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻ አከናወኑ ።ትራምፕ ከአዲሱ የፕሬዚደንታዊ ምርጫ ውድድር አጋራቸው ጋር የከፍተኛ ፉክክር መናገሻ ወደ ሆነችው ሚችጋን ግዛት ተመልሰዋል ።
"ልክ የዛሬ ሳምንት ፣ በዚሁ ሰዓት እና ደቂቃ ነበር . . . " ሲሉ በመጀመር ጆሯቸውን በደም ለውሶ ፣ አንድ ደጋፊያቸውን ገድሎ ሁለቱን ስለ አቆሰለው የሀምሌ 13ቱ (እኤአ) የፔንሳልቪያኒያ ተኩስ ጥቃት ዙሪያ ለታዳሚው አጋርተዋል ።
"ከፊታችሁ የቆምኩት በፈጣሪ ክብር ብቻ ነው ! " ያሉት ትራምፕ ፣ ጆሯቸው ተሸፍኖበት የነበረው ነጭ ፋሻ ፣ የቆዳቸውን ቀለም በሚመሳሰል መሸፈኛ መተካቱን ተናግረዋል ።
ትራምፕን የኦሆሃዮው ግዛት ሴናተር ጄ . ዲ ቫንስ የተቀላቀሏቸው ሲሆን ፣ ሁለቱም ሚልዋኪ በተደረገው የሪፐብሊካኑ ብሔራዊ ጉባዔ ላይ የፓርቲው ዕጩዎች ይፋ ከተደረገ በኃላ በጋራ የተገኙበት የመጀመሪያው መድረክ ሆኗል ።
ሚቺጋን በህዳር ወር የሚካሄደውን ፕሪዚደንታዊ ምርጫ ውጤት ይወስናሉ ተብለው ከሚጠበቁ የፓርቲ የበላይነት የሚቀያየርባቸው ግዛቶች መካከል አንዷ ናት ። ትራምፕ በአውሮፓዊያኑ 2016 ምርጫ በ10ሺ ድምጾች በጠባብ ክፍተት የግዛቲቱን አብላጫ ድምጽ አሸንፈዋል ። ሆኖም ዲሞክራቱ ጆ ባይደን ወደ ፕሬዚደንትነት ባመሩበት የአውሮፓዊያኑ 2020 ድሉን በመገልበጥ ትራምፕን በ150ሺ ድምጾች በመብለጥ የግዛቲቱን አብላጫ ድምጽ አሸንፈዋል ።
ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ በተገኘበት የምረጡኝ ቅስቀሳ ንግግራቸው ላይ ትራምፕ ፣ ህገ ወጥ ስደተኞችን በገፍ እንደሚያባርሩ እና በፖለቲካ ጠላቶቻቸው ላይ የብቀላ እርምጃ እንደሚወስዱ ሲዝቱ ቢሰሙም ለዴሞክራሲ አደጋ ስለመሆናቸው እና ስለ ጽንፈኝነታቸው ይነዛሉ ያሏቸውን ጥረቶች ግን አስተባብለዋል ።
በትራምፕ ሁለተኛ የስልጣን ዘመን ፖሊሲ እና ግላዊ ዕቅድ ላይ ከሚያተኩረው ፣ በቀድሞ የአስተዳደራቸው ባለስልጣናት ከተረቀቀው የሄሪቴጅ ፋውንዴሽን "ዕቅድ 2025" በድጋሚ ራሳቸውን ለማግለል ሞክረዋል ።
የባይደን የምርጫ ዘመቻ ዒላማ የሆነውን ዕቅድ " የከረረ ቀኝ ዘመምነት " ፣ " በእጅጉ ጽንፈኛ" - "ልክ እንደ ጽንፈኛ ግራ ዘመሞች " ሲሉ አውግዘውታል ። ስለ ጉዳዩ እንዳማያውቁም አጽንኦት ሰጥተዋል (ኤፒ)።
መድረክ / ፎረም