በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ናይሮቢ ውስጥ የተቃውሞ ሰልፍ ማካሄድ ተከለከለ


ፎቶ ፋይል፦ በናይሮቢ ኬንያ እአአ ግንቦት 2/2023
ፎቶ ፋይል፦ በናይሮቢ ኬንያ እአአ ግንቦት 2/2023

የኬንያ ፖሊስ በዋና ከተማዋ ናይሮቢ ላልተወሰነ ጊዜ የተቃውሞ ሰልፍ መከልከሉን አስታወቀ፡፡

የተቃውሞ ሰልፎች በሰላማዊ መንገድ መከናወናቸውን ለማረጋገጥ የአመራር ችግር አለብን የሚል ምክንያት የሰጠው ፖሊስ ዛሬ ሐሙስ ክልክላውን ያወጀው ተቃዋሚዎች ፕሬዚደንቱ ሥልጣን እንዲለቅቁ በመጠየቅ ጽሕፈት ቤታቸው ደጃፍ ሰልፍ ለማካሄድ ካወጡት እቅድ በጥቂት ሰዓታት ቀደም ብሎ መሆኑን አሶሲየትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

ተጠባባቂ የፖሊስ ዋና ተቆጣጣሪው ዳግላስ ካንጃ ባወጡት መግለጫ ያለው የአመራር እጥረት የጸጥታ ሥርዓት ማስከበር ላይ ችግር ፈጥሯል ማለታቸው ተመልክቷል፡፡ በሰሞኑ የተቃውሞ ሰልፎች በርካታ የንግድ ድርጅቶች ተዘርፈዋል፡ ተቃጥለዋል፡፡

ዛሬ ናይሮቢ ውስጥ አልፎ አልፎ የተቃውሞ ሰልፈኞች የታዩ ሲሆን ወደ ፕሬዚደንቱ ጽህፈት ቤት የሚወስዱት ዋና ዋና ጎዳናዎች ተዘግተዋል፡፡

ባለፈው ሰኔ ወር መጀመርያ የግብር ጭማሪ የሚያስከትለው የፋይናንስ ረቂቅ ህግ እንዳይጸድቅ በመጠየቅ በተጀመረው እና ለአንድ ወር በዘለቀው የተቃውሞ ሰልፍ ቢያንስ 50 ሰዎች መገደላቸውን የሀገሪቱ የሰብዓዊ መብቶች ኮምሽን አስታውቋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG