በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተባብሶ የቀጠለው የሱዳን የፖለቲካ ቀውስ


ከመካከለኛው ሱዳን ገዚራ ግዛት ወደ ምስራቃዊ ሱዳን ገዳረፍ ከተማ የሚመጡት የተፈናቀሉ ዜጎች ሱዳናዊ ቤተሰቦች ሲያስተናግዷቸው እአአ ሰኔ 3/2024
ከመካከለኛው ሱዳን ገዚራ ግዛት ወደ ምስራቃዊ ሱዳን ገዳረፍ ከተማ የሚመጡት የተፈናቀሉ ዜጎች ሱዳናዊ ቤተሰቦች ሲያስተናግዷቸው እአአ ሰኔ 3/2024

ቁጥራቸው 50,000 የሚጠጋ ሱዳናውያን በምስራቃዊ ሱዳኗ ገዳሪፍ መጠለላቸውን እና በመጪዎቹ ቀናት ውስጥም ‘ተጨማሪ ተፈናቃዮች ይደርሳሉ’ ብለው እንደሚጠብቁ የዩኒሴፍ ባለ ሥልጣናት ትላንት አስታወቁ።

የዓለም አቀፉ የሕጻናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ የፕሮግራም አስተባባሪ ሲናገሩ፤ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ማዕከል ካለፈው ሃምሌ 2 አንስቶ 400 ሕጻናትን መመዝገቡን አመልክተዋል። ወደ ነፃ ምርጫ በሚደረግ ሽግግር እና ተዋጊ ኃይሎችን የማዋሃድ እርምጃዎች ከተመለከቱ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ፤ በሱዳን ጦር ሠራዊት እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መካከል ባለፈው ዓመት የሚያዝያ ወር የተቀሰቀሰውን ውጊያ ተከትሎ 25 ሚሊዮን ሕዝብ .. ከሱዳን ሕዝብ ገሚስ ያህሉ ማለት ነው - እርዳታ የሚሻ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባለ ሥልጣናት ይፋ አድርገዋል። የረሃብ አደጋ እያንዣበበ መሆኑን ያስጠነቀቁት ባለሥልጣናት አክለውም 10 ሚሊዮን ሱዳናውያን ቀያቸውን ጥለው መሰደዳቸውን አመልክተዋል።

በሌላ ዜና የሰላማዊ ዜጎችን ደሕንነት ለማስጠበቅ እና ለተረዎች የነብስ እርዳታ ማድረስ የሚያስችል ሁኔታ ለመፍጠር ለታለመ የተኩስ አቁም ስምምነት ተፋላሚውን ወገኖች ለማደራደር ላለፈው ሃሙስ ጄኔቫ ላይ ተይዞ ለነበረው በመንግሥታት ድርጅት የተመራ ድርድር አንደኛው ወገን ብቻ መገኘቱ ተገልጧል። የትኛው ወገን ሳይገኝ እንደቀረ የተጠየቀው ጄኔቫ የሚገኘው የመንግሥታቱ ድርጅት ጽ/ቤት ቃል አቀባይ ግን የቡድኑን ማንነት ይፋ ከማድረግ ተቆጥበዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG