በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሞቃዲሾው ምግብ ቤት በደረሰው የቦምብ ጥቃት የሞቱት ሰዎች ቁጥር ዘጠኝ ደረሰ


የአካባቢው ሰዎች ፍንዳታው በደረሰበት ቦታ ከወደሙ ተሽከርካሪዎች ፍርስራሽ አጠገብ ተሰበሰበዋል፡፡
የአካባቢው ሰዎች ፍንዳታው በደረሰበት ቦታ ከወደሙ ተሽከርካሪዎች ፍርስራሽ አጠገብ ተሰበሰበዋል፡፡

የአውሮፓ እግር ኳስ የዋንጫ ግጥሚያ በመመልከት ላይ በነበሩበት የሞቃዲሾ ምግብ ቤት ላይ በመኪና ላይ በተጫነ ቦምብ በደረሰው ጥቃት የሞቱት ሰዎች ቁጥር ዘጠኝ መድረሱን የጸጥታ ምንጮች አመለከቱ፡፡

ትናንት ቀደም ብሎ የሀገሪቱ መንግሥት የሰለባዎቹ ቁጥር አምስት መሆኑ ያስታወቀ ሲሆን የሶማሊያ የብሔራዊ ጸጥታ ቢሮ ባለስልጣን መሐመድ ዩሱፍ ለአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ በሰጡት ቃል ዘጠኝ ሰዎች እንደሞቱ እና ሌሎች ሃያ ሰዎች እንደቆሰሉ ተናግረዋል፡፡

የሚበዙት ወጣቶች የሆኑት ታዳሚዎች የእግር ኳስ ግጥሚያውን በማየት ላይ እንዳሉ ቦምብ የተጫነው መኪና ጥሶ በመግባት ባደረሰው ፍንዳታ ብዙዎቹ እንደምንም ለማምለጥ እንደቻሉ ባለስልጣኑ ተናግረዋል፡፡

ለጥቃቱ ኅላፊነት የወሰደ አካል ባይኖርም የመንግሥቱ የዜና አገልግሎት ተጠያቂው አልሻባብ ነው ብሏል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG