በኢትዮጵያ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚያስተምሩ መምህራን ክፍያቸው ካለው የኑሮ ሁኔታ (ውድነት) ጋር የሚጣጣም ባለመሆኑ መቸገራቸውን ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል፡፡
ኑሮ የከበዳቸው መምህራን ሙያውን እየተው በሌሎች የስራ መስኮች ላይ መስማራት መጀመራቸውንና ተመራቂ ተማሪዎችም ሙያውን ለመቀላቀል ፍላጎት እያጡ መምጣታቸውን ይናገራሉ፡፡
የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር በበኩሉ ጥያቄያቸው ምላሽ እንዲያገኝ ሲሰራ መቆየቱን ገልጾ አሁንም መንግስትን በመወትወት ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡
በዚህ ጉዳይ ላይ ከትምህርት ሚንስቴር ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያድምጡ፡፤
መድረክ / ፎረም