በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሩሲያ እና በዩክሬን የድሮን ጥቃት ልውውጥ የሩሲያ የነዳጅ ማከማቻ ነደደ


ዩክሬን ኪቭ ሐምሌ 2016
ዩክሬን ኪቭ ሐምሌ 2016

በሩሲያ ደቡብ ምዕራባዊ ሮስቶቭ ክልል ዛሬ ቅዳሜ ጠዋት ዩክሬን በረጅም ርቀት ተወንጫፊ በፈጸመችው የድሮን ጥቃት የነዳጅ ዘይት ማከማቻ በእሳት መያያዙን የአካባቢው ባለስልጣናት ገልጸዋል።

ባለፉት ጥቂት ወራት ዩክሬን የክሬምሊንን የጦር አቅም ለማዳከም በሩሲያ የነዳጅ ዘይት ማከማቻዎች ላይ የምታደርጋቸውን የአየር ጥቃቶች አጠናክራለች።

የሞስኮ የጦር ሰራዊት በምስራቃዊ ዩክሬን ያለውን ጥቃቱን መጨመሩን ተከትሎ በጦርነቱ ሦስተኛ ዓመት የመሳሪያ እጥረት አጋጥሞታል። ይኸም የሩሲያ ወታደሮችን ለጥቃት አጋልጧል።

የሮስቶቭ ክልል ሀገረ ገዥ ቫስሊ ጎሉቤቭ የድሮን ጥቃቱ እስከ 200 ሜትር ርቀት የተጓዘ የእሳት ነበልባል አስነስቷል ብለዋ። እሳቱ መነሳቱ ከተገለጸ ከአምስት ሰዓታት በኋላም መጥፋቱን ጨምረው አስታውቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG