በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቢኒያም ግርማይ የቱር ደ ፍራንስ 12ኛውን ደረጃ ውድድር አሸነፈ


ኤርትራዊው ቢኒያም ግርማይ
ኤርትራዊው ቢኒያም ግርማይ

ኤርትራዊው ቢኒያም ግርማይ ከጥቂት ሰዓታት በፊት ተደርጎ የነበረውን የቱር ደ ፍራንስ የብስክሌት ውድድር 12ኛ ደረጃ በአሸናፊነት አጠናቋል።

በፈረንሣይ በመካሄድ ላይ ባለው የብስክሌት ውድድር ለሶስተኛ ጊዜ ያሸነፈው ቢኒያም፣ በተወዳጁ ዓለም አቀፍ የብስክሌት ውድድር ያሸነፈ የመጀመሪያ ጥቁር አፍሪካዊ ነው።

በሶስተኛውና በስምንተኛ ደረጃ ውድድሮች ያሸነፈው ቢኒያም ዛሬ በተደረገው 12ኛ ደርጃ ውድድርም በአሸናፊነት አጠናቆ፣ በአረንጓዴ ማሊያ ምድብ 328 ነጥብ በማግኘት እየመራ ይገኛል።

ውድድሩ 21 ደረጃዎች ሲኖሩት በቀሪዎቹ ቀናት ዘጠኝ ውድድሮች ይካሄዳሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG