በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጆሐንስበርግ ውስጥ አውቶቡስ ተገልብጦ 12 ተማሪዎች ሞቱ


ጆሐንስበርግ ከተማ ደቡብ አፍሪካ
ጆሐንስበርግ ከተማ ደቡብ አፍሪካ

ደቡብ አፍሪካ ጆሐንስበርግ ከተማ አቅራቢያ ዛሬ ረቡዕ አስራ ሁለት ተማሪዎች ወደትምሕርት ቤት ለመሄድ የተሳፈሩበት መለስተኛ አውቶቡስ (ሚኒበስ) ተገልብጦ መሞታቸው ተገለጠ፡፡ ከሌላ ተሽከርካሪ ጋር ከተጋጨ በኋላ በተገለበጠው መለስተኛ አውቶቡስ ላይ ቃጠሎ መነሳቱን ባለስልጣናት አመልክተዋል፡፡

ሙሉ በሙሉ በእሳት አደጋው በወደመው መኪና ውስጥ ሕይወታቸው ያለፈው ልጆች የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች መሆናቸው ተገልጿል፡፡ ሌሎች ጉዳት የደረሰባቸው ሰባት ልጆች ወደሆስፒታል መወሰዳቸው የተገለጸ ሲሆን ፖሊስ አደጋውን እየመረመረ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ደቡብ አፍሪካ በአፍሪካ አህጉር በመንገድ መገናኛ ረገድ ትልቅ ዕድገት ካስመዘገቡ ሀገሮች መካከል ብትሆንም በመንገድ ደሕንነት ረገድ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ካሉ ሀገሮች መካከል አንዷ መሆኗ ተገልጿል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG