በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሞስኮ ላይ የሰላም ጥሪ ያሰሙት ሞዲ ‘በጦርነቱ የሚያልቁት ሕጻና ጉዳይ ልብ ይሰብራል’ አሉ


የሕንዱ ጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ፤ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በሞስኮ ክሬምሊን፣ እአአ ሐምሌ 9/2024
የሕንዱ ጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ፤ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በሞስኮ ክሬምሊን፣ እአአ ሐምሌ 9/2024

በሞስኮ ጉብኝታቸው ወቅት የሰላም ጥሪ ያሰሙት የሕንዱ ጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ በዩክሬይኑ ጦርነት የሚገደሉት ሕፃናት ጉዳይ እጅግ አሳዛኝ መሆኑን ገልጠው፤ የጦርነቱ መቋጫ ከጦር አውድማ እንደማይገኝ ተናግረዋል።

ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ያላቸውን ቁርጠኝነት አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩት ሁለቱ መሪዎች፤ ሩስያ ዩክሬይንን ከወረረችበት እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር የካቲት 2022 ወዲህ የመጀመሪያቸው የሆነውን ጉባኤ ዛሬ አካሂደዋል። የሞዲ አስተያየት የተሰማው ዩክሬን ሩስያን ተጠያቂ ያደረገችበት በኪዬቭ የሚገኘው ዋናው የሕፃናት ሆስፒታል በሚሳኤል ጥቃት ከተመታ አንድ ቀን በኋላ ነው።

ሌሎች በርካታ የዩክሬይን ከተሞች በተመቱበት ከባድ ጥቃት 31 ሰዎች ተገድለዋል። በቴሌቭዥን በተላለፈ አስተያየታቸው ከክሬምሊን ባሰሙት ንግግር "ጦርነት ይሁን ግጭት፣ ወይም የሽብር ጥቃት፣ በሰው ልጅ የሚያምን ሁሉ የሰው ህይወት ሲጠፋ ሕመም ይሰማዋል” ያሉት ሞዲ “ነገር ግን ንፁሃን ሕጻናት ሲገደሉ .. ‘ንፁሃን ሕጻናት ሲሞቱ ስናይ’ ልብ የሚሰብር እና ሥቃዩም የበረታ ነው” ብለዋል

ሕንድ በቀጠናው ያለው ሁኔታ ወደ ቀድሞ ሰላሙ እንዲመለስ “በሁሉም መንገድ” ለመተባበር ዝግጁ መሆኗን ያረጋገጡት ሞዲ “በቦምብ፣ በጠብ መንጃ እና በጥይት መሃል መፍትሔዎች እና የሰላም ንግግሮች አይሳኩም” ብለዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG