በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን ሀገር ለመምራት የሚያስችል አዕምሯዊ እና አካላዊ ጥንካሬ እንዳላቸው ተናገሩ


ባይደን ሀገር ለመምራት የሚያስችል አዕምሯዊ እና አካላዊ ጥንካሬ እንዳለቸው ተናገሩ
ባይደን ሀገር ለመምራት የሚያስችል አዕምሯዊ እና አካላዊ ጥንካሬ እንዳለቸው ተናገሩ

በፖለቲካዊ ህይወት 5 አስርት ዓመታትን ያሳለፉት እና በድጋሚ ምርጫ ዘመቻ ጫፍ ላይ የሚገኙት ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ፣ ተቀናቃኛቸው የቀድሞውን ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕን አሸንፈው ሀገሪቱን ለተጨማሪ አራት ዓመታት ለመምራት የሚያበቃ ስል አዕምሮ እና የአካል ብርታት እንዳላቸው ተናገሩ ።

ባይደን ከአቢሲ ቴሌቭዥን ጣቢያ ጋዜጠኛ ጆርጅ ስቴፋኖጳውሎስ ጋር በነበራቸው እና ትናንት አርብ በመላ ሀገሪቱ በተላለፈ ቃለ መጠይቅ ላይ ነው ንግግራቸው የተሰማው ።


"ለስራው በእጅጉ ብቁ የሆንኩ ሰው ነኝ ። ነገሮችን መከወን እችልበታለሁ " ያሉት ባይደን ፣ ቀደም ብሎ የመካከለኛው ምዕራብ አሜሪካ የምርጫ አውድማ በሆነችው ዌስኮንሲን በተካሄደ ፣ 300 ያህል ደጋፊዎቻቸው በተገኙበት የድጋፍ ሰልፍ ላይ በምርጫው እንደሚቆዩ ማረጋገጫ ሰጥተዋል ።


አንዳንድ ዴሞክራት ህግ አውጪዎች በግል ፣ አንዳንዴም በይፋ ፣ የ81 ዓመቱ ባይደን ለቀጣይ አራት ዓመታት ሀገሪቱን ማስተዳደር ይቅርና አራት ወራት ከቀሩት የምርጫ ቀን በፊት ትራምፕን ለመገዳደር የሚያበቃ የአዕምሮ እና የአካል ብቃት በመጠራጠር ያላቸውን ስጋት ሲገልጹ ቆይተዋል ።


ባይደን ግን ፣ ለስቴፋኖጳውሎስ ፣" የሁሉ ባለቤት ጌታ ወርዶ 'ጆ ሆይ ከውድድሩ ውጣ' ቢለኝ ኖሮ ከውድድሩ እወጣ ነበር ። እስካሁን ግን አልወረደም።" ሲሉ መልሰዋል ።

ባይደን ከሳምንት በፊት ከትራምፕ ጋር ክርክር ባደረጉበት ወቅት በግራ መጋባት ውስጥ ሆነው አንዳንዴም ንግግራቸውን ድንገት ሲያቆሙ መታየታቸውን ተከትሎ በዲሞክራቶች ዘንድ የባይደን የስልጣን ጊዜ ወደ ማብቂያ እየተቃረበ ነው የሚል ስጋት ጨምሯል።

ባይደን ግን በክርክሩ ምሽት በጉንፋን ምክንያት ተዳክመው እና መልካም ስሜት ውስጥ እንዳልነበሩ በመጥቀስ ፣ ለደካማ ብቃታቸው ተጠያቂ ራሳቸው መሆናቸውን ተናግረዋል ።

ባይደን በትናንት ምሽቱ ቃለ ምልልሱ ወቅት ንቁ ከመሆናቸው በተጨማሪ የጋዜጠኛውን ጥያቄ ካለማመንታት ሲመልሱ አምሽተዋል ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG