በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለኢትዮጵያ እግር ኳስ እድገት የአፍሪካውያን ቀደምት ታላላቅ ተጫዋቾች ምክር


ለኢትዮጵያ እግር ኳስ እድገት የአፍሪካውያን ቀደምት ታላላቅ ተጫዋቾች ምክር
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:46 0:00

ካኑን ጨምሮ በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደረጉ የቀድሞ አፍሪካውያን ታዋቂ የእግር ኳስ ተጫዋቾች፣ አገሪቱ እግር ኳሷን ለማሳደግ በወጣቶች ላይ አተኩራ እንድትሠራ መክረዋል፡፡

ከትላንት በስቲያ ዐርብ፣ ሰኔ 21 ቀን ጀምሮ ለሦስት ቀናት በዐዲስ አበባ ከተማ በተካሔደው “ሸነን” የተሰኘ የፋሽን ፌስቲቫል ላይ ለመታደም ወደ ኢትዮጵያ የመጡት አፍሪካውያኑ ስመጥር የቀድሞ እግር ኳስ ተጫዋቾች፣ ዛሬ እሑድ፣ ሰኔ 23 ቀን 2016 ዓ.ም.፣ ከጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አሕመድ ጋራ የወዳጅነት ጨዋታ አድርገዋል፡፡

በወዳጅነት ፓርክ በተካሔደው በዚኹ ጨዋታ፣ ዓለም ከሚያውቃቸው አፍሪካውያን የቀድሞ ከዋክብት መካከል የኾኑት ናይጄሪያውያኑ ንዋንኩ ካኑ፣ ዳንኤል አሞካቺ እና ታሪቦ ዌስት፣ እንዲሁም ሴኔጋላዊው ሄንሪ ካማራ ተሳትፈዋል፡፡

ናይጄሪያዊው ካኑ፣ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጠው አስተያየት፣ ኢትዮጵያ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ)ን ከመሠረቱት አገራት አንዷ እንደኾነች አውስቶ፣ እምባዛም የማትታወቅበትን የእግር ኳሷን ለማሳደግ ግን በአዳጊዎች ላይ መሥራት እንደሚጠበቅባት ምክሩን ለግሷል፡፡

የእንግሊዙን አርሰናልን ጨምሮ በተለያዩ ታላላቅ የአውሮፓ ክለቦች በአጥቂ መሥመር የተጫወተው ካኑ፣ የእርሱ እና መሰል ቀደምት ታዋቂ ተጫዋቾች ጉብኝት፣ ለኢትዮጵያውያን ወጣት የእግር ኳስ ተጫዋቾች የራሱ ፋይዳ እንዳለው አስረድቷል፡፡

በወዳጅነት ፓርክ የተካሔደውን የወዳጅነት ጨዋታ በመሀል ዳኝነት የመራው ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማም፣ የቀድሞ ታላላቅ አፍሪካውያን ተጫዋቾች ጉብኝት ስለሚኖረው ፋይዳ አስተያየት ሰጥቶናል፡፡

ታዋቂዎቹን ተጫዋቾች ጨምሮ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የመጡት ጎብኚዎቹ፣ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ከካቢኔያቸው ጋራ በመኾን በወዳጅነት አደባባይ ችግኞችንም ተክለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG