በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል ሊባኖስ ላይ ጥቃት ከፈጸመች ትጠፋለች ስትል ኢራን አስጠንቀቀች


ሂዝቦላ ወደ እስራኤል ያስወነጨፋቸው ሮኬቶች ሰኔ 2016 ዓ.ም
ሂዝቦላ ወደ እስራኤል ያስወነጨፋቸው ሮኬቶች ሰኔ 2016 ዓ.ም

ኢራን እስራኤል በሊባኖስ ላይ ጥቃት ካደረሰች ኢራን ከቀጠናዊ አጋሮቿ ጋር በመሆን “በሁሉም የተቃውሞ ግንባር” እስራኤልን ትጋፈጣለች ስትል ዛሬ ቅዳሜ አስጠንቅቃለች።

በኒውዮርክ ከሚገኘው የኢራን ልዑክ የተሰማው ይህ አስተያየት በእስራኤል እና በሂዝቦላ ከምትደገፈው ሊባኖስ ጋር የሚኖረው ግጭት ሰፊ የሆነ ቀጠናዊ ጦርነት ሊፈጠር ይችላል የሚል ስጋት አስከትሏል።

ከሁለቱም ወገኖች ጸብ አጫሪ የሆኑ የጎንዮሽ ልውውጦች በዚህ ወር ተባብሰው ቀጥለዋል። የእስራኤል ጦር በሊባኖስ ላይ ጥቃት የመሰንዘር ዕቅዶቹ ተቀባይነት ማግኘታቸውን ያረጋገጠ ሲሆን፤ በአንጻሩ ሂዝቦላህ በሚከፍተው የአጸፋ ምላሽ የትኛውም የእስራኤል አካል እንደማይተርፍ አስጠንቅቋል።

የኢራን ተልዕኮ በኤክስ ማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ገጹ ላይ ባሰፈረው ጽሁፍ “የጽዮናዊው መንግስት በሊባኖስ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር የሚያደርገውን ፕሮፓጋንዳ እንደ ስነ ልቦናዊ ጦርነት ይቆጠራል” ብሏል።

ጽሁፉ አክሎም ነገር ግን "ሙሉ ወታደራዊ ጥቃት ከተጀመረ፣ አውዳሚ ጦርነት ይከተላል” ያለ ሲሆን አያይዞም “የሁሉም ተቃዋሚ ግንባር ሙሉ ተሳትፎን ጨምሮ ሁሉም አማራጮች በጠረጴዛው ላይ ናቸው" ብሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG