የዩናይትድ ስቴትስ ጦር በቀይ ባህር ሶስት የሁቲ ሰው አልባ ጀልባዎችን ማውደሙን ትላንት ቅዳሜ አስታወቀ፡፡
የአሜሪካ ጦር ሃይሎች በቀይ ባህር ላይ በ 24 ሰዓታት ውስጥ በኢራን የሚደገፉ ሶስት የሁቲ ሰው አልባ ጀልባዎች ማውደማቸውን የዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ ዕዝ ትላንት ቅዳሜ አስታውቋል።
በሌላም በኩል ዩናይትድ ስትቴስ ሁቲ በአውሮፕላን አጓጓዥ መርከብ ላይ አድርሻለሁ ያለው ጥቃት 'በፍፁም ውሸት' ነው ብላለች፡፡
ሁቲዎች ሶስት ፀረ-መርከቦች ባለስቲክ ሚሳኤሎችን ወደ ኤደን ባህረ ሰላጤ ማስወንጨፋቸው ሲገለጽ በአሜሪካ ፣ በጋራ ኃይሉም ሆነ የንግድ መርከቦች ላይ ግን የደረሰ ምንም አይነት ጉዳት አለመኖሩ ተገልጿል፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ማእከላዊ ዕዝ በአውሮፕላን ተሸካሚ ድዋይት ዲ.አይዘንሃወር መርከብ ላይ የሁቲ ሃይሎች በቅርቡ የተሳካ ጥቃት አድርሰናል ያሉት “ሙሉ ለሙሉ ውሸት” ነው ሲል ውድቅ አድርጎታል።
መድረክ / ፎረም