በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩቶ ከወጣቶቹ ተቃዋሚዎች ጋር ለመነጋገር ዝግጁ ነኝ አሉ


የኬንያ ወጣቶች በፋይናንስ ጉዳይ የሚከራከሩ አባላት በሚገኙበት ምክር ቤት ህንጻ ፊት የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደዋል ፤ እኤአ ሰኔ 18 2024
የኬንያ ወጣቶች በፋይናንስ ጉዳይ የሚከራከሩ አባላት በሚገኙበት ምክር ቤት ህንጻ ፊት የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደዋል ፤ እኤአ ሰኔ 18 2024

የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በዚህ ሳምንት የታክስ ጭማሪን በመቃወም በሀገር አቀፍ ደረጃ ሰላማዊ ሰልፍ ካደረጉ በሺዎች ከሚቆጠሩ ወጣት ተቃዋሚዎች ጋር "ለመነጋገር" ዝግጁ መሆናቸውን የፕሬዚዳንቱ ቃል አቀባይ ዛሬ እሁድ ተናግረዋል።

ሰልፉን በማህበራዊ ሚዲያ በቀጥታ ስርጭት እያስተላለፉ ባካሄዱ ወጣት ኬኒያውያን የሚመራው ተቃውሞ በሩቶ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ላይ ቅሬታ እየፈጠረ መምጣቱ መንግስትን አስጨንቋል፡፡

ፕሬዚዳንት ሩቶ "ወጣቶቻችን በአገራቸው ጉዳይ ላይ በመሳተፍ ወደ ፊት ተራምደዋል። ድምጻቸው እንዲሰማ በመቆም ዴሞክራሲያዊ ግዴታቸውን ተወጥተዋል፣ እኔ ኮርቼባቸዋለሁ” ሲሉ መናገራቸውን የፕሬዝዳንቱ ቃል አቀባይ ሁሴን መሀመድ በቀድሞው ትዊተር በአሁኑ X ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ አስተላልፈዋል፡፡

ሩቶ "ችግሮቻችሁን ለይተን እንደ ሀገር በጋራ ለመስራት ከእናንተ ጋር ውይይት እናደርጋለን" ሲሉም ስለ ተቃውሞ ሰልፎቹ የመጀመሪያቸው የሆነውን የህዝብ አስተያየት ሰጥተዋል።

በዋና ከተማዋ ናይሮቢ ባላፈው ሀሙስ በተካሄዱ ሰልፎች ሁለት ሰዎች ሲሞቱ በርካታ ሰዎች ቆስለዋል ሲሉ የመብት ተሟጋቾች ገልጸዋል።

የተቃውሞ ሰልፎቹ በአብዛኛው ሰላማዊ የነበሩ ቢኾንም፣ ፖሊስ አስለቃሽ ጋዝ እና ውኃ በመርጨት በምክር ቤቱ አካባቢ የነበሩ ተቃዋሚዎችን ለመበተን ሙከራ ማድረጉ ተነግሯል፡፡

በኬንያ ወጣቶች መሪነት የተነሣሣውና ባለፈው ማክሰኞ በናይሮቢ ተጀምሮ በመላ አገሪቱ የተሰራጨው ተቃውሞ፣ በመጭው ማክሰኞ እ.ኤ.አ ሰኔ 25 ቀን ብሔራዊ የሥራ ማቆም አድማ እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል፡፡

የሩቶ አስተዳደር የመንግሥትን ገቢ ለመጨመር የታቀደው ታክስ በውጭ ብድር ላይ ያለውን ጥገኝነት ለማስቆም አስፈላጊ መሆኑን በመግለጽ ተከላክሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG