በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኒጀር በቻይና የሚደገፈው የነዳጅ ማስተላለፊያ ችግር ገጠመው


የኒጀር ነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት በጸጥታ ችግር ተሰናክሏል
የኒጀር ነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት በጸጥታ ችግር ተሰናክሏል

በኒጀር በቻይና የሚደገፈው የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት በውስጥ የጸጥታ ችግር እና ከቤኒን ጋር በተፈጠረ ዲፕሎማሲያዊ ውዝግብ ስጋት ውስጥ ገብቷል፡፡

ሁለቱም ችግሮች ባለፈው ዓመት የተካሄደውን መፈንቅለ መንግስት ተከትለው የተፈጠሩ ናቸው፡፡

ከኒጀር ወደ ቤኒን ኮቶኑ ወደብ የሚሄደው 1,930 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር፣ የኒዠርን የነዳጅ ምርት በአምስት እጥፍ ገደማ ለማሳደግ ታስቦ ከቻይና ብሔራዊ የነዳጅ ኩባንያ ጋር፣ በ400 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት የተወጠነ ፕሮጀክት ነው።

የማስተላለፊያው መስመር ዝርጋታ ሥራ ከቤኒን ጋር በተፈጠረ ዲፕሎማሲያዊ አለመግባባት እና በአካባቢው የአርበኞች ነፃ አውጪ ግንባር ቡድን በተፈጸመ ጥቃት ባላፈው ሳምንት ቆሟል፡፡

አማፂው ቡድን ባላፈው ሳምንት በሰነዘረው ጥቃት ማስተላለፊያውን በከፊል ማሰናከሉ ሲነገር ከቻይና ጋር ያለው ስምምነት እስካልተሰረዘ ድረስ ተጨማሪ ጥቃቶችን እንደሚያደርስ አስፈራርቷል፡፡

ቀድሞውንም ችግር የነበረበት የኒጀር ፀጥታ ወታደራዊ ጁንታ ሀገሪቱን ከተቆጣጠረ በኋላ በሳላህ መሀሙድ የሚመራው አማፂ ቡድን ብረት በማንሳቱ ተጨማሪ ስጋት ፈጥሯል፡፡

ከቤኒን ጋር ዲፕሎማሲያዊ ውዝግብ የጀመረው፣ የኒጀር ፕሬዝዳንት በመፈንቅለ መንግስት ከስልጣን ከተወገዱ በኋላና ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ድንበሮቻቸው መዝጋታቸውን ተከትሎ ነው፡፡

የነዳጅ ፕሮጀክቱን አደጋ ላይ የሚጥል የሀገር ውስጥ ነፃ አውጪ ቡድንም የተመሰረት ሲሆን ቤኒን ይህን ቡድን ትደግፋለች፡፡

ኒጀር ከፈረንሳይ ጋር ያላትን ወታደራዊ ግንኙነት ካቋረጠች በኋላ ቤኒን ድንበሯን ክፍት አድርጋለች፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG