በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር በዋሽንግተን ስለ ጋዛና ሊባኖስ ይመክራሉ


የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት
የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት በጋዛ ጦርነት እና ግጭቱ እንዳይስፋፋ ስጋት ባሳደረው በሊባኖስ ድንበር በኩል ባለው የተኩስ ልውውጥ ጉዳይ ለመወያየት ዛሬ እሁድ ወደ ዋሽንግተን መጥተዋል።

የጋዛ ጦርነት ከጀመረበት ከስምንት ወራት በፊት አንስቶ በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ በኢራን የሚደገፈው ሂዝቦላ ከእስራኤል ጋር ተኩስ እየተለዋወጠ ነው።

ጋላንት እስራኤል በጋዛ፣ ሊባኖስ እና ሌሎች አካባቢዎች ርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቷን በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሩ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲን እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከንን ጨምሮ የአሜሪካ ባለስልጣናትን እንደሚያገኙም አስታውቀዋል ።

እስራኤል የሂዝቦላህ ከፍተኛ አዛዥን መግደሏን ተከትሎ በሰኔ ወር ሂዝቦላ በእስራኤል ከተሞች እና ወታደራዊ ቦታዎች ላይ ከፍተኛ ጥቃት ሰንዝሯል፡፡

የአሜሪካ ልዑክ አሞስ ሀችስቴይን በእስራኤልና ሊባኖስ ድንበር አካባቢ እየተባባሰ የመጣውን የተኩስ ልውውጥ እና የንግግር ውጥረት ለማርገብ ባላፈው ሳምንት እስራኤልን እና ሊባኖስን ጎብኝተዋል።

አንዳንድ የእስራኤል ባለስልጣናት በጋዛ ራፋህ አካባቢ የሃማስ እስላማዊ ተዋጊዎች የመጨረሻ ጦር ነው ባሉት ሚሊሻ ላይ በማነጣጠር የሚያደርጉትን ወታደራዊ ዘመቻቸውን በሊባኖስ ሊከሰቱ ከሚችሉ እርምጃዎች ጋር ያያይዙታል።

ባለሥልጣናቱ በጋዛ የሚደረገውን ወታደራዊ ዘመቻ አፋፍሞ ማጠናቀቅ ሠራዊቱን በሂዝቦላህ ላይ ሊወሰድ ለሚችለው ጥቃት ነጻ ኃይል ያደርገዋል ብለዋል፡፡

ይህን ተከትሎ የሚካሄደው ሶስተኛው ወታደራዊ ዘመቻ የጋዛን ጦርነት በማስቆም አካባቢውን ማረጋጋት የወደመውን መልሶ መገንባት እንደሆነም ባለሥልጣናቱ ተናግረዋል፡፡

ጋላንት በእነዚህ እቅዶች ዙሪያ ከዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ጋር እንደሚመክሩ አስታውቀዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG