በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና እና ፈረንሳይ በጋራ ሳተላይት አመጠቁ


የፈረንሳይ እና የቻይና የጋራ ሳተላይት ሰኔ 2016
የፈረንሳይ እና የቻይና የጋራ ሳተላይት ሰኔ 2016

የፈረንሳይ-ቻይና የጋራ ሳተላይት በህዋ ውስጥ ሊፈጠር የሚችል ከፍተኛ ፍንዳታን ለማጥናት ዛሬ ቅዳሜ ወደ ህዋ መጥቃለች። ይህ ጥረትም በአውሮፓ እና በእስያ ኃይሎች መካከል ሊደረግ የሚችል የኃይል ትብብር ጉልህ ተምሳሌት ተደርጎ ታይቷል።

በሁለቱ ሀገራት መሃንዲሶች የተሰራችው ሳተላይት በህዋ ውስጥ ያሉ የጋማ ጨረር አፍላቂዎችን ለመፈለግ ከመሬት በቢሊዮን የሚቆጠሩ የብርሃን ዓመታትን ርቃ እንደምትጓዝ ተገልጿል።

ሁለት የፈረንሳይ እና ሁለት የቻይና ሮኬቶችን የያዘችው ሳተላይት በቻይና ሰሜን ምዕራብ ሲችዋን ግዛት ከሚገኘው ዢቻንግ የሳተላይት ማምጠቂያ ትተኮስ በስፍራው ተገኝተው ማየታቸውን የአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ጋዜጠኞች ዘግበዋል።

መርሃ ግብሩ በፈረንሳይ እና በቻይና የህዋ ሳይንስ ተቋማት መካከል እና በሌሎች የሳይንስ እና የቴክኒካል ቡድኖች መካከል ትብብር እንዲኖር ያደረገ ነው። ይሁን እንጂ በዚህ ደረጃ ያለ የምዕራቡ ዓለም እና የቻይና የህዋ ላይ ትብብር፤ በተለይም በጎርጎርሳዊያኑ 2011 ዩናይትስ ስቴትስ በናሳ የሳይንስ ጣቢያ እና በቤጂንግ መካከል ምንም ዓይነት ትብብር እንዳይኖር ማገዷን ተከትሎ ያልተለመደ መሆኑ ተዘግቧል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG