በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አንድ የእስራኤል ዜጋ በዌስት ባንክ ተተኩሶበት ሞተ


ዌስት ባንክ ሰኔ 2016
ዌስት ባንክ ሰኔ 2016

ግጭት እየተስፋፋባት ባለው የፍልስጤም ግዛት በሆነችው በሰሜን ዌስት ባንክ፤ በዛሬ ዕለት አንድ የእስራኤል ዜጋ ተተኩሶበት ሞቶ መገኘቱን የእስራኤል ወታደራዊ ኃይል አስታውቋል። ቃልቂሊያ በተሰኘችው እና የእስራኤል ሰራዊቶች በሚንቀሳቀሱባት ከተማ ሟቹ መገኘቱን ተገልጿል። መግለጫው በዛሬው ዕለት በዌስት ባንክ ሁለት ታጣቂዎች በእስራኤል ኃይሎች ከተገደሉ በኋላ ነው የወጣው።

ይሁን እንጂ ምንም ዓይነት ተጨማሪ መረጃ ለህዝብ ይፋ አልተደረገም።

የእስራኤል እና ሃማስ ጦርነት በጥቅምት ወር ከተጀመረ አንስቶ በዌስት ባንክ ግጭት እያያየለ መጥቷል። ከዛን ጊዜ አንስቶ 549 ፍልስጤማዊያን በእስራኤል መገደላቸውን የአካባቢውን ሞት የሚመዘግበው የፍልስጤም የጤና ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል። በተመሳሳይ በዌስት ባንክ የሚገኙ ፍልስጤማዊያን አምስት ወታደሮችን ጨምሮ ዘጠኝ እስራኤላዊያንን መግደላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መረጃ ያሳያል።

በዌስት ባንክ ይዞታ ስር በምትገነው ቃልቂሊያ እና በሌሎች የዌስት ባንክ አካባቢዎች የእስራኤል ዜጎች እንዳይገቡ ክልክል ነው።

በሚያዚያ ወር 2016 ዓ.ም በ 14 ዓመቱ እስራኤላዊ ዐዳጊ ሰፋሪ ላይ በፍልስጤም ግዛት የተፈጸመው ጥቃት በፍልስጤም ግዛት ባሉ ሰፋሪዎች ላይ ጥቃቶች እንዲከታተሉ ማድረጉ ተዘግቧል። የእስራኤል ወታደራዊ ኃይል ዐዳጊው ተገድሎ ነው ያለ ሲሆን፤ ይህን ተከትሎ ከግድያው ጋር ተያያዥነት ያላቸው ፍልስጤማዊያን መታሰራቸው የሚታወስ ነው

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG