ከጋምቤላ ከተማ ወደ ኑዌር ዞን የትራንስፖርት አገልግሎት በመቋረጡ፣ የኑዌር ዞን ተጓዦች ለችግር መዳረጋቸውን ተናገሩ፡፡
የዞኑ ተጓዦች ይጠቀሙበት የነበረው የኒውላንድ መናኸርያ ተዘግቶ፣ ሁሉም ተጓዦች በዋናው መናኸርያ እንዲጠቀሙ በክልሉ መንግሥት መወሰኑን የገለጸው የትራንስፖርት ቢሮው በበኩሉ፣ ኾኖም ኑዌር ተጓዧች በጸጥታ ስጋት ምክንያት በዋናው መናኸርያ ለመገልገል ባለመፈለጋቸው ችግሩ ማጋጠሙን አስታውቋል፡፡ መንግሥት ይህን ውሳኔ ከማሳለፉ በፊት፣ በአኙዋክ እና በኑዌር ማኅበረሰቦች መካከል እርቀ ሰላም መፍጠር እንደበረበትም ተመልክቷል።
ከነዋሪዎቹ ስለሚሰማው ቅሬታ እና የጸጥታ ስጋት በተመለከተ፣ ከጋምቤላ ከተማ ከንቲባ አቶ ጋልዋክ ጋች ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለዛሬ አልተሳካም፡፡
መድረክ / ፎረም