በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከሊባኖስ ጋር በድንበር ውጥረት ውስጥ ያለችው እስራኤል ጋዛን ደበደበች


ጋዛ ሰኔ 2016
ጋዛ ሰኔ 2016

በሰሜናዊ እስራኤል የሊባኖስ አዋሳኝ ድንበር ላይ ውጥረት እየተባባሰ ባለበት ሁኔታ የእስራኤል ሃይሎች ጋዛን በመምታት ከሃማስ ታጣቂዎች ተዋግተዋል። የእስራኤል እና የሀማስ የእርቅ ጥረት መሻሻል አለማግኘቱ ተገልጿል።

ምስክሮች እስራኤል በደቡባዊ የራፋህ ከተማ እና በማዕከላዊ የጋዛ ሰርጥ ጥቃቶች መፈጸሟን አስታውቀዋል። በቡረጂ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ በማዕከላዊ ዴየር አል ባላህ ከተማ በተፈጸመ ጥቃት የ11 ዓመት ልጅ ህይወቱ ማለፉን ተከትሎ በአል-አቅሳ የሰማዕታት ሆስፒታል ስዎች ተሰባሰበው ታይተዋል።

የእስራኤል ጦር ሰራዊት በዘይቱን አካባቢ የሚገኘውን የታጣቂውን ህዋስ ለማጥቃት በማዕከላዊ ጋዛ ተልዕኳቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቋል።

እማኞች ጋዛን ከግብጽ በሚያገናኘው ደቡባዊ ድንበር በራፋህ እስራኤል በሄሊኮፍተር ጥቃት መፈጸሟን ሲናገሩ ሀማስ በበኩሉ ታጣቂዎቹ በታል አል-ሱልጣን አካባቢ በሚገኙ የእስራኤል ወታደሮች ላይ በሞርታት ጥቃቶች መፈጸሙን ገልጿል።

በሌላ በኩል በመካከለኛው ምስራቅ ግጭት እንዳያንሰራራ ከፍተኛ ስጋት አለ። መቀመጫቸውን ሊባኖስ ያደረጉት እና በኢራን የሚደገፉት የሄዝቦላህ ተዋጊዎች ሀማስን በመደገፍ በእስራኤል የወታደራዊ ዒላማዎች ላይ ሮኬት እና የሚሳይል ናዳዎችን መተኮስ ጀምረዋል።

ሄዝቦላ በዚህ ሳምንት ከረቡዕ እለት አንስቶ እስራኤል ከጦር መሪዎቹ መካከል አንዱን በመግደሏ የበቀል ጥቃት መጀመሩን አስታውቋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG