በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በማላዊው የአውሮፕላን አደጋ ምክትል ፕሬዚዳንት ሳሎስ ቺሊማ ሞቱ


ፎቶ ፋይል፦ የማላዊ ምክትል ፕሬዚዳንት ሳሎስ ቺሊማ
ፎቶ ፋይል፦ የማላዊ ምክትል ፕሬዚዳንት ሳሎስ ቺሊማ

ትላንት ሰኞ የ51 ዓመቱን ምክትል ፕሬዚዳንታቸውን ሳውሎስ ቺሊማን እና ሌሎች ዘጠኝ ሰዎች አሳፍሮ ይበር የነበረው ወታደራዊ አውሮፕላን በመከስከሱ አሳፍሯቸው የነበሩ ሰዎች በሙሉ ማለቃቸውን የማላዊ ፕሬዝዳንት ዛሬ አስታወቁ።

ወደ ሰሜናዊቷ የምዙዙ ከተማ በማቅናት ላይ የነበረው አውሮፕላን ጭጋግ በበዛበት መጥፎ የአየር ሁኔታ ውስጥ ማረፍ ባለመቻሉ ወደ ዋና ከተማዋ ሊሎንግዌ እንዲመለስ ከተነገረው በኋላ ነው፤ ለጊዜው የገባበት ሳይታወቅ ቆይቶ የመከስከሱ ዜና በነፍስ አድን ሠራተኞች ተረጋግጧል።

ድንገቱን “እጅግ አሰቃቂ አደጋ” ሲሉ የገለጡት ፕሬዚዳንት ላዛሩስ ቻክዌራ ለሃገሪቱ ሕዝብ ባሰሙት ንግግር የነፍስ አድን ሠራተኞች ተሳፋሪዎቹ በሙሉ ያለቁበትን አውሮፕላን ፍርስራሽ ማግኝታቸውን በመጠቆም “በቃላት ለመግለጽ የሚያዳግት አሳዛኝ አደጋ” ብለውታል።

አንድ የጦር ሰራዊቱ የነፍስ አድን ሠራተኞች ቡድን አባል ለኤኤፍፒ ባጋሯቸው የፎቶግራፍ ምስሎች የሰራዊቱ አባላት ዶርኒል 228-202 የተባለ አንድ የማላዊ አየር ኃይል አውሮፕላን ፍርስራሽ ካለበት በጭጋግ የተሸፈነ ኮረብታማ ሥፍራ ላይ ቆመው ያሳያል።

ትላንት ከጠዋቱ 3 ሰዓት ላይ ከሊሎንግዌ የተነሱት የአውሮፕላኑ ተሳፋሪዎች በአንድ የቀድሞ የካቢኔ ሚንስትር የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ለመገኘት 370 ኪሎ ሜትሮች ርቃ ወዳለችው ምዙዙ በማቅናት ላይ ነበሩ። በአደጋው ከሞቱት ውስጥ የቀድሞዋ የማላዊ ቀዳማይ እመቤት ሻኒል ዲዚምቢሪም እንደሚገኙበት ታውቋል።

በሌላ በኩል እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2014 ለመጀመሪያ ጊዜ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት ቺሊማ በማላዊ ሕዝብ ይልቁንም ደግሞ ከወጣቶች ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነት አትርፈው ነበር። ይሁንና እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2022 ለሁለተኛ ጊዜ ከተመረጡ በኋላ ከአንድ የብሪታንያ እና የማላዊ ዜግነት ካላቸው የንግድ ሰው ጋር በተገናኘ የጉቦ ቅሌት ተወንጅለው መታሰራቸው እና ሥልጣናቸውን መገፈፋቸው ይታወቃል። ሆኖም ባለፈው ወር የማላዊ ፍርድ ቤት የቀረበባቸውን ክስ ሙሉ በሙሉ ውድቅ ካደረገ በኋላ ወደ ቀድሞ ሥልጣናቸው ተመልሰው ነበር።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG