በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በዳርፉር ብቸኛው ሆስፒታል ላይ ጥቃት ሰነዘረ


ፋይል - በሱዳን እየጨመረ በመጣው ጥቃት የተፈናቀሉ ነዋሪዎች በምዕራብ ዳርፉር፣ ማስተሪ በተሰኘች መንደር ውስጥ በችኮላ በተወጠሩ ድንኳኖች ውስጥ ብርድልብስ አንጥፈው ተቀምጠው ይታያሉ- ሐምሌ 30፣200
ፋይል - በሱዳን እየጨመረ በመጣው ጥቃት የተፈናቀሉ ነዋሪዎች በምዕራብ ዳርፉር፣ ማስተሪ በተሰኘች መንደር ውስጥ በችኮላ በተወጠሩ ድንኳኖች ውስጥ ብርድልብስ አንጥፈው ተቀምጠው ይታያሉ- ሐምሌ 30፣200

በሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ የሰሜን ዳርፉር መዲና በሆነችው ኤል ፋሸር ከተማ ላይ ያደረሰውን ጥቃት ተከትሎ፣ በአካባቢው የሚገኘው ብቸኛው ሆስፒታል እንዲዘጋ ማስገደዱን አንድ ዓለም አቀፍ ሆስፒታል አስታውቋል። ኃይሉ በሆስፒታሉ ሠራተኞችና ታካሚዎች ላይ ተኩስ መክፈቱን እና መዝረፉን ድንበር የለሹ የሐኪሞች ቡድን አስታውቋል።

በሰሜን ዳርፉር የምትገኘው ኤል ፋሸር በምዕራባዊ ክልል በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ቁጥጥር ሥር ያለወደቀች ብቸኛ ከተማ የነበረች ሲሆን፣ ለሰብዓዊ ዕርዳታ መተላለፊያ ቁልፍ ቦታ ነበረች፡፡ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በዳርፉር ክልል በሱዳን ሠራዊት ቁጥጥር ሥር የምትገኘውን ብቸኛ ከተማ ለመያዝ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ነው።

ባለፈው ወር ከተማዋን ለመቆጣጠር በተደረገው የሁለት ሣምንታት ውጊያ 120 ሠዎች መገደላቸው ታውቋል።
በሆስፒታሉ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ ታካሚዎች፣ የሆስፒታሉ ሠራተኞች እንዲሁም የድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድኑ አባላት ማምለጥ መቻላቸው ሲታወቅ፣ በጥቃቱ የተጎዱ ሰዎች ስለመኖራቸው ለጊዜው ማወቅ እንዳልተቻለ ቡድኑ አስታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG