በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢራን አፈጉባኤ በፕሬዚዳንትነት ለመወዳደር ተመዘገቡ


ፋይል፡ የኢራን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ መሀመድ ቃሊባፍ ግንቦት 20 2012 ለአፈጉባኤ በተመረጡበት ወቅት
ፋይል፡ የኢራን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ መሀመድ ቃሊባፍ ግንቦት 20 2012 ለአፈጉባኤ በተመረጡበት ወቅት

የኢራን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ መሀመድ ቃሊባፍ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ በሄሊኮፕተር አደጋ መሞታቸውን ተከትሎ ለሰኔ 28ቱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እጩነታቸውን አስመዝግቡ ።

ወግ አጥባቂው ቃሊባፍ የራይሲን ፖሊሲዎች ለመቀጠል እና፣ በዓለም አቀፍ ማዕቀቦች ውስጥ ቁልፍ ችግሮች ሆነዋል ያሏቸውን ድህነትን እና የዋጋ ንረትን ለመፍታት ቃል ገብተዋል፡፡

የኢራን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ይስተካከላሉ ብለው ካላመኑ እንደማይወዳደሩም ቃሊባፍ ተናግረዋል።

በቅርቡ የፓርላማ አፈ-ጉባኤ ሆነው በድጋሚ የተመረጡት ቃሊባፍ ቀደም ሲል እኤአ ከ2005 እስከ 2017 የቴህራን ከንቲባ ሆነው አገልግለዋል ።

እ.ኤ.አ. በ2005 እና 2013 ለፕሬዝዳንትነት ተወዳድረው ያልተሳካላቸው ሲሆን፣ እኤአ ከ2017 ምርጫ ራሳቸውን በማግለል ለሟቹ ፕሬዝዳንት ራይሲ የቅስቀሳ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ለምርጫው ራሳቸውን ካጩት ሌሎች ታዋቂ እጩዎች መካከል የቀድሞው ፕሬዝዳንት ማህሙድ አህመዲን ነጃድ፣ የቀድሞ የፓርላማ አፈ ጉባኤ አሊ ላሪጃኒ፣ የቀድሞ የማዕከላዊ ባንክ ሀላፊ አብዶልናስር ሄማቲ እና የቀድሞ የኒውክሌር ተደራዳሪ ሰኢድ ጃሊሊ ይገኙበታል።

ሁሉም እጩዎች የወግ አጥባቂው የበላይ ጠባቂ ምክር ቤት እጩነታቸው እስከሚያጽድቅበት እኤአ ሰኔ 11 ድረስ መጠበቅ ይኖርባቸዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG