በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዘለንስኪ የእስያ ሀገራት በስዊዘርላንድ የሰላም ጉባዔ ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቀረቡ


የዩክሬኑ ፕሬዘዳንት ቮልደሚየር ዘለንስኪ በሻንጋሪ ላ የእስያ የጦር መሪዎች ጉባዔ ላይ ግንቦት 2016
የዩክሬኑ ፕሬዘዳንት ቮልደሚየር ዘለንስኪ በሻንጋሪ ላ የእስያ የጦር መሪዎች ጉባዔ ላይ ግንቦት 2016

የዩክሬኑ ፕሬዘዳንት ቮልደሚየር ዘለንስኪ ዛሬ እሁድ በሻንጋሪ ላ የእስያ ሀገራት የመከላከያ መሪዎች ጉባዔ ላይ ተገኝተው መሪዎቹ በመጭው የጎርጎርሳዊያኑ ሰኔ 15 እና 16 በስዊዘርላንድ የሚደረገው የሰላም ጉባዔ ላይ መሪዎቹ እንዲሳተፉ ጥሪ አድርገዋል።

ዘለንስኪ በሲንጋፖር ሻንጋሪ ላ ጉባዔ ባደረጉት ቁልፍ ንግግር ሦስተኛ ዓመቱን በያዘው የዩክሬን ሩሲያ ጦርነት ዩክሬን ለዲፕሎማሲን ለማስጠበቅ የምታደርገው ጥረት ላይ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

"ከረጅም ጊዜ በፊት፣ ዓለም የተበታተነች መስሎ ነበር ታይቶኝ ነበር፤ ነገር ግን አብዛኛዎቹ ሀገራት ቢያንስ የጋራ ደህንነትን በተመለከተ እውነተኛ ሰላምን እንደሚመኙ እና መተባበር እንደሚችሉ አይተናል” በማለት በመቶዎች ለሚቆጠሩ የእስያ ቀጠናዊ ልዑካን እና መሪዎች ንግግር አድርገዋል።

ቻይና ከዘንድሮው የስዊዘርላንድ የሰላም ጉባዔ እራሷን አግልላለች። ቻይና የሰላም ጉባዔው ለመገለል የወሰደችውን ውሳኔም በተመለከተ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማኦ ኒንግ በጎርጎሮሳዊያኑ ግንቦት 31/2024 ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ሩሲያ እና ዩክሬን ሁለቱም በስብሰባው ላይ መሳተፍ አለባቸው በማለት በቻይና የቀረበውን ቅድመ ሁኔታ ጉባዔው ባለሟሟላቱ ቻይና ከጉባዔው እራሱን ማግለሏን አስታውቀዋል።

የጀርመኑ ቻንስለር ኦላፍ ሹልዝ እና የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮንን ጨምሮ በርካታ የአውሮፓ መሪዎች ቻይና ለሩሲያ የጦር ሃይል የምታደርገውን ድጋፍን በተመለከተ ስጋታቸውን የገለጹ ሲሆን፤ በተጨማሪም ቤጂንግ የሰላም ሂደትን ለማመቻቸት ተጽዕኖዋን እንድትጠቀም አሳስበዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG