በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ናይጄሪያ ህገወጥ የመዓድን ቁፋሮን ለማስቆም ከፍተኛ ጥረት ጀመረች


በናይጄሪያ ጆስ መዓድን አውጭዎች
በናይጄሪያ ጆስ መዓድን አውጭዎች

የናይጄሪያ መንግስት ህገ-ወጥ የማዕድን ቁፋሮዎችን በመቆጣጠር ከሚያዝያ ወር አንስቶ ለኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች፣ ስማርት ስልኮች እና የሃይል ባትሪዎች የሚያገለግለውን ሊቲየም የተሰኘ ወሳኝ ማዕድን በመስረቅ ላይ የሚገኙ በደርዘን የሚቆጠሩ ፍቃድ አልባ የማዕድን ቆፋሪዎችን አስሯል።

በቅርቡ የታሰሩት የናይጄያ ህገወጥ መዓድን ቆፋሪዎች ሁኔታም ናይጄሪያ ወሳኝ ማዕድናትን የማውጣት ስራዋን ለመቆጣጠር፣ ህገወጥ እንቅስቃሴን ለመግታት እና ከማዕድን ሀብቷ የተሻለ ጥቅም ለማግኘት የምታደርገው ጥረት አካል መሆኑ ተገልጿል። የንፁህ የሃይል አቅርቦት ሽግግር፣ ከከሰል ድንጋይ፣ ከዘይት እና ከጋዝ ወደ ታዳሽ ሃይል እና ባትሪዎች የሚደረግ ሽግግር የአለም አቀፍ የሊቲየም፣ የቲን እና ሌሎች ማዕድናት ፍላጎት እንዲንር አድርጓል።

በናይጄሪያ የሙስና ቁጥጥር ዝቅተኛ መሆን እና አብዛኞቹ የማዕድን ክምችቶች አነስተኛ የመንግስት ቁጥጥር ባሉባቸው ራቅ ያሉ አካባቢዎች መገኘታቸው ህገ ወጥ የመዓድን ቁፋሮዎች እንዲያይል ማድረጉ ተገልጿል። የናይጄሪያ ባለሥልጣናት ከሕገወጥ ማዕድን ማውጣት ልማዶች የሚገኘው ትርፍ በሰሜናዊ ናይጄሪያ ክፍል የሚገኙ የሚሊሻ ቡድኖችን ለማስታጠቅ እያገዘ ነው ብለዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG