በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደቡብ አፍሪካ የዓለም አቀፉን ፍርድ ቤት ውሳኔ አደነቀች


ደቡብ አፍሪካ የመሰረተችውን የእስራኤል ፍልስጤማውያን ክስ ጉዳይ የሚመለከተው ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት (ፎቶ ሮይተር)
ደቡብ አፍሪካ የመሰረተችውን የእስራኤል ፍልስጤማውያን ክስ ጉዳይ የሚመለከተው ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት (ፎቶ ሮይተር)

ዓለም አቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት እስራኤል በጋዛ ከተማ ራፋህ የምታደርገውን ጥቃት እንድታቆም የሰጠውን ትዕዛዝ ደቡብ አፍሪካ አደነቀች፡፡

ፍርድ ቤቱ ያቀረበውን የተኩስ አቁም ጥሪ ያደነቁት የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናሌዲ ፓንዶር ትላንት ዓርብ በሬዲዮ በሰጡት አስተያየት የተባበሩት መንግስታት አባል ሀገራት ለውሳኔው ተግባራዊነት ድጋፍ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

ደቡብ አፍሪካ ሀማስ ጥቅምት 7 ቀን በእስራኤል ላይ ያደረሰውን ጥቃት ተከትሎ እስራኤል በጋዛ የወሰደችውን እርምጃ “ዘር ማጥፋት” ነው ስትል ከሳለች።

ዓለም አቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት የዘር ማጥፋት የተባለውን ጉዳይ እያጤነ ሲሆን ቀደም ሲል እስራኤል በወታደራዊ ዘመቻዋ ወቅት የዘር ማጥፋት ድርጊቶችን ለመከላከል መውሰድ ይገባታል ያለውን የቅድመ ዝግጅት እርምጃዎችን አውጥቷል።

እስራኤል ግን በራፋህ ወታደራዊ እምርጃዋን የቀጠለች በመሆኑ ደቡብ አፍሪካ ተጨማሪ ትዕዛዞች እንዲወጡ ጠይቃለች፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ፓንዶር እስራኤል የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ስለማክበሯ ያላቸውን ጥርጣሬ ገልጸው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና የጸጥታው ምክር ቤት ዓለም አቀፍ ህግን እንዲያስከብሩ ጠይቀዋል ሲል ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG