በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና በታይዋን አቅራቢያ የጦር ልምምድ አደረገች


የቻይና ወታደራዊ መርከብ ከግሪን ደሴት በስተደቡብ ምስራቅ ጥቂት ማይል ርቀት በታይዋን ምስራቃዊ የባህር ጠረፍ ላይ (እኤአ ግንቦት 24 ቀን 2024)
የቻይና ወታደራዊ መርከብ ከግሪን ደሴት በስተደቡብ ምስራቅ ጥቂት ማይል ርቀት በታይዋን ምስራቃዊ የባህር ጠረፍ ላይ (እኤአ ግንቦት 24 ቀን 2024)

ቻይና 111 የጦር አውሮፕላኖችን እና 46 የባህር ኃይል መርከቦችን በማሰማራት በታይዋን ዙሪያ ለሁለት ቀናት የፈጀውን ወታደራዊ ልምምድ አጠናቃለች።

የታይዋን መከላከያ ሚኒስቴር 82 የቻይና የጦር አውሮፕላኖች የታይዋንን የባህር ሰርጥ መስመር አቋርጠው ወደ ታይዋን የውሃ ክልል 24 ማይል ቀርበው መብረራቸውን አስታውቋል፡፡

ልምምዱ ቻይና እንደ ገንጣይ በምትመለከታቸው አዲሱ የታይዋን ፕሬዝደንት ላይ ቺንግ-ቴን ላይ ያነጣጠረ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የጋራ የባህር-አየር ፍልሚያ ዝግጁነት፣ የጦር ሜዳ ቅኝትና እና ኢላማዎችን በትክክል በመምታት ላይ ያተኮሩ ልምምዶች የተካተቱበት መሆኑም ተዘግቧል፡፡

ቤጂንግ ልምምዶቹን “አስፈላጊ ናቸው” ስትል ታይዋን “አለመረጋጋትን የሚፈጥሩ ትንኮሳዎች ናቸው” ብላለች።

ተንታኞች ይህ የቻይና ልምምድ ከነሀሴ 2022 ወዲህ ሶስተኛው መጠነ ሰፊ ልምምድ ሲሆን ወደ ታይዋን የቀረበ እንደሆነም ጠቁመዋል።

የቻይናን ጥቃት ለመከላከል ታይዋን ደህንነቱ የተጠበቀ የአሜሪካ ፀረ-መርከብ ሚሳዬሎች ያስፈልጋታል ሲሉም ተንታኞቹ መክረዋል፡፡

የቻይና መከላከያ ሚኒስቴር ውህደቱ እስኪሳካ ድረስ ቀጣይነት ያለው ጫና እንደሚኖር አስጠንቅቋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG