በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ህንድ እየመረጠች ነው፣ ሞዲ ለሶስተኛ ጊዜ ይወዳደራሉ


መራጮች በህንድ
መራጮች በህንድ

የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ለሶስተኛ ጊዜ የሥልጣን ዘመን መወዳደር በሚፈልጉበት ባለብዙ ደረጃዎች ምርጫ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህንዳውያን ዛሬ ቅዳሜ ድምጻቸውን ሰጥተዋል።

መራጮቹ ድምጻቸውን የሰጡት በስምንት ክልሎች እና በፌዴራል ግዛቶች በሚገኙ 58 የምርጫ ክልሎች 45 ዲግሪ ሴልሺየስ የደረሰ ከፍተኛ የሙቀት መጠን በተመዘገበበት ሁኔታ ውስጥ እንደነበር ተጠቅሷል፡፡

የሞዲ ብሃራቲያ ጃናታ ፓርቲ (ቢጄፒ) ከተቃዋሚዎቹ ከኮንግሬስ ፓርቲ እና ከክልላዊ ፓርቲዎች ጥምረት ጋር በመወዳደር ያሸንፋል ተብሎ ይጠበቃል።

ተችዎች እስልምናና ሙስሊሞችን ይቃወማሉ የሚባሉት ሞዲ በምርጫ ዘመቻቸው ከፋፋይ ንግግሮችን ተጥቀመዋል ሲሉ ወቅሰዋቸዋል፡፡

ሞዲ በታችኛው ምክር ቤት ከ543 መቀመጫዎች 400 በማግኘት ለማሸነፍ እንዳለሙ ተነግሯል፡፡

ተቃዋሚዎች በስራ አጥነት እና በዋጋ ንረት የተነሳ ሊያሸነፉ እንደሚችሉ ተስፋ አድርገዋል፡፡

የምርጫው የመጨረሻ ዙር እኤአ ሰኔ 1 እንደሚካሄድ ሲነገር ውጤቱ ሰኔ 4 እንደሚገለጽ ይጠበቃል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG