በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከታገዱ የሩሲያ ሀብቶች በሚገኝ ወለድ ዩክሬንን ለመርዳት ታስቧል


የቡድን ሰባት ገንዘብ ሚኒስትሮች ስብሰባ በጣልያን (ፎቶ ሮይተርስ)
የቡድን ሰባት ገንዘብ ሚኒስትሮች ስብሰባ በጣልያን (ፎቶ ሮይተርስ)

ዛሬ ቅዳሜ ጣልያን ውስጥ የተሰበሰቡት የበለጸጉት የቡድን 7 ሀገራት የገንዘብ ሚኒስትሮች ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች ከሚገኘው ወለድ ዩክሬንን ለመርዳት ይስማማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ስምምነቱ በሚቀጥለው ወር ለሚደረገው የቡድን 7 ሀገራት መሪዎች ውሳኔ ጥርጊያ መንገድ እንደሚከፍት ተገምቷል፡፡

ውሳኔው ያስፈለገው ከሁለት ዓመታት በላይ ሩሲያን እየተጋፈጠች ለምትገኘው ዩክሬን ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ በማስፈለጉ ነው፡፡

የዩክሬን የገንዘብ ሚኒስትር ሰርጊ ማርቼንኮ በሰሜን ጣልያን በምትገኘው ስትሬሳ ከተማ በተካሄደው የሚኒስትሮቹ ስብሰባ የገንዘብ ድጋፍ ጠይቀዋል፡፡

ኪቭ በካርኪቭ ክልል የሩሲያን ግስጋሴ“አቁሜያለሁ” ብትልም የዩክሬን ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ዛሬ ቅዳሜ “ጠላት በከፊልም ቢሆን ስኬት አግኝቷል” ሲሉ “ሁኔታው አስጨናቂ ነው” ብለዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የግምጃ ቤት ሹም ጃኔት ዬለን ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች ከሚገኘው የወደፊት ወለድ ለዩክሬን የ50 ቢሊዮን ዶላር ብድር እንዲሰጥ አማራጭ አቅርበዋል፡፡

ዋሽንግተን ትላንት ዓርብ ለኪቭ አዲስ የ275 ሚሊዮን ዶላር ወታደራዊ እርዳታ እንደሚሰጥ አስታውቃለች፡፡

የቀረበው ሀሳብ ዩክሬንን በትልቁ የሚያጠናክር ቢሆንም እዳውን የሚወስነው ማነው ፣ ሊኖር የሚችለውን ኪሳራስ በዩናይትድ ስቴትስ እና ቡድን ሰባት ሀገሮች መካከል መከፋፈል የሚቻለው እንዴት ነው? የወለድ ተመኑ አወሳሰንስ እንዴት ይሆናል? የሚሉትን ጨምሮ ዝርዝር ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡

ሩሲያ ዩክሬንን እኤአ በ2022 ከወረረች ወዲህ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ዶላሮች፣ መዋዕለ ንዋዮችና ሌሎች ንብረቶች በምዕራባውያን ታግደዋል፡፡ ለዩክሬን እንዲከፈል የታሰበው በተቀማጭ ከተያዙ እነዚህ ሀብቶች መሆኑ በኤ.ኤፍ.ፒ ዘገባ ተመልክቷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG