በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ማኅበራዊ የትስስር ገጾች በፊልም ሥራ ሞያዊነት ላይ የደቀኑት አደጋ በጥበበኞች እይታ


ማኅበራዊ የትስስር ገጾች በፊልም ሥራ ሞያዊነት ላይ የደቀኑት አደጋ በጥበበኞች እይታ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:55 0:00

ማኅበራዊ የትስስር ገጾች በፊልም ሥራ ሞያዊነት ላይ የደቀኑት አደጋ በጥበበኞች እይታ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በማኅበራዊ የትስስር መድረኮች፣ በተለይም በዩቲዩብ እና በቲክቶክ ድረ ገጾች፣ ተሠርተው በሚቀርቡ የፊልም እና አጫጭር ድራማዎች ይዘቶች ላይ ቅሬታዎች እየተሰሙ ናቸው፡፡

መድረኮቹ፣ ሁሉም ሰው ፊልም ሠሪ እንዲኾን የፈጠሩት ዕድል፣ የፊልም ሞያ ሥነ ምግባርን እና የማኅበረሰብን ዕሴት ያልጠበቁ ይዘቶች እንዲበራከቱ አንዱ ምክንያት ስለመኾኑ የአሜሪካ ድምፅ በጉዳዩ ላይ ያናገራቸው የጥበቡ ባለሞያዎች ያስረዳሉ፡፡

በርግጥ፣ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች ለፊልም ጥበብ ያመጡት ዕድል መኖሩን ባለሞያዎቹ ሳይገልጹ አላለፉም፡፡ ኾኖም፣ ሐያስያን እንዲበራከቱ በማድረግ ተመልካቾች የሚያዩትን ይዘት እንዲመርጡ ማበረታታት፣ አቀራረቡን ለመግራት ያስችላሉ ብለው እንደሚያስቡ ያመለክታሉ፡፡

አስማማው አየነው የፊልም ባለሞያዎቹን ቤዛ ኀይሉንና ሔኖክ አየለን አነጋግሮ ተከታዩን አዘጋጅቷል፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይመልከቱ፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG