በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስና የኒጀር መከላከያ ሚኒስቴር የጋራ መግለጫ አወጡ


የዩናይትድ ስቴትስ እና የኒጀር ባንዲራ 2010 ዓ.ም
የዩናይትድ ስቴትስ እና የኒጀር ባንዲራ 2010 ዓ.ም

ከዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስቴር ተወካዮች እና ከኒጀር ሪፐብሊክ ብሔራዊ መከላከያ የተውጣጡ ተወካዮች ከረቡዕ ግንቦት 07 / 2016 እስከ ዛሬ እሁድ ግንቦት 11/ 2016 ዓ.ም ድረስ በኒጀር ሪፐብሊክ ኒሜይ የጋራ ስምምነት ኮሚሽን አካል በመሆን በመገናኘት ተወያይተዋል። ሁለቱ አካላት የዩናይትድ ስቴትስ ሰራዊትን ከኒጀር ሪፐብሊክ ሥርዓት ባለውና በአስተማማኝ መንገድ የሚወጣበት መንገድ በማስተባበር ዙሪያ ነው የተወያዩት ሲል በጋራ ያወጡት መግለጫ ያስታወቀ ሲሆን በሠራዊቱ መካከል የተደረገው ውይይት በሁለቱ ወገኖች መካከል ፍጹም ግልጽነት እና ፍፁም የሆነ መከባበር በተሞላበት ሁኔታ ነበር የተካሄደው ብሏል።

ከዩናይትድስቴትስ በኩል የመከላከያ ሚኒስትሩ ልዑካን የተመራው በልዩ ተልዕኮዎች እና የዝቅተኛ ግጭቶች ረዳት የመከላከያ ሚኒስቴር ሚንስተር በሆኑት ክሪስቶፈር ማየር እና የሀላፊዎች የጋራ አለቃና የጋራ ሃይል ልማት ዳይሬክተር ሌተናል ጄኔራል ዳግቪን አንደርሰን ሲሆን በኒዠር በኩል የብሔራዊ መከላከያ ሚኒስቴር የልዑካን ቡድን በሠራዊቱ ዋና አዛዥ ኮሎኔል-ሜጀር ማማኔ ሳኒ ኪያዎ በድርድሩ ላይ ተሳትፈዋል።

በሁለቱ አካላት መካከል በተደረገው ውይይት ሁለቱ ሃይሎች የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ሰራዊት ቀድሞ ስምምነት ላይ በተደረሰው መሰረት እስከ መጪው የጎርጎሮሳዊያኑ መስከረም 15/2024 ከኒጀር ለቆ የሚወጣበትን ሁኔታ በተመለከተ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

ሁለቱም ልዑካን የአሜሪካ ኃይሎች ከኒጀር በሚወጡበት ወቅት የጥበቃ እና የደህንነት ዋስትናቸው እንደሚጠበቅ አረጋግጠዋል። በተጨማሪም ልዑካን ቡድኑ ወደ አሜሪካ የሚገቡትን እና የሚወጡበትን ሂደት የሚያመቻች አሰራርን መዘርጋታቸው በመግለጫው የሰፈረ ሲሆን ይህም ለወታደራዊ በረራዎ እና ከመጠን በላይ የጫኑ በረራዎችን እንዲሁም የአየር የማረፊያ ፍቃድን ጨምሮ ያካተተ ስምምነት መድረሳቸውን የጋራ መግለጫው ጠቁሟል።

የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስቴር እና የናይጄሪያ ብሔራዊ መከላከያ ሚኒስቴር የናይጄሪያ እና የአሜሪካ ኃይሎች በጥምረት መስዋዕትነት የከፈሉትን ሽብርተኝነትን የመዋጋት ተልዕኮ በማስታወስ የናይጄሪያን ጦር ኃይሎችን ለመገንባት ለተደረገው ጥረት እርስ በርስ ይመሰጋገናሉ ሲል መግለጫው ጨምሮ አስታውቋል። ሁለቱ አካላት በጋራ ጥቅም ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ትብብር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።

የአሜሪካ ኃይሎች ከኒጀር መውጣታቸው የዩናይትስ ስቴትስ-የኒጀርን የልማት ግንኙነት ቀጣይነት ላይ ተጽዕኖ እንደማያመጣም መግለጫው አክሎ አስታውቋል። ዩናይትድ ስቴትስ እና ኒጀር የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን የወደፊት እጣ ፈንታ በተመለከተ ውሳኔ ላይ ለመድረስ ቀጣይነት ያለው ዲፕሎማሲያዊ ውይይት ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናቸውም የጋራ መግለጫው አስታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG