በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢራን ሁለት ሴቶችን ጨምሮ ሰባት ሰዎችን በስቅላት ቀጣች


የስቅላት ቅጣት በኢራን
የስቅላት ቅጣት በኢራን

ኢራን ዛሬ ቅዳሜ ሁለት ሴቶችን ጨምሮ ቢያንስ ሰባት ሰዎችን በስቅላት ሞት ቀጥታለች ሲል የኢራን ሰብአዊ መብቶች ድርጅት አስታወቀ፡፡

"የሞት ቅጣቷን እያጠነከረች በምትገኘው እስላማዊት ሪፐብሊኳ ኢራን አነስተኛ ቁጥር ያላቸው የአይሁድ ማህበረሰብ አባላት ከፍተኛ አደጋ ውስጥ ይገኛሉ" ሲልም መሰረቱን በኖርዌይ ያደረገው ለትርፍ ያልተቋቋመው የኢራን ሰብአዊ መብቶች ድርጅት አስታውቋል፡፡

ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ ከአደገኛ ህጾች ጋር በተያያዙ ወንጀሎች ከተከሰሱ አምስት ሰዎች ጋር በኡርሚያ እስር ቤት ውስጥ ከተሰቀሉት መካከል የሁለት ታዳጊ ልጆች እናት የሆኑት የ53 ዓመቷ ፓርቪን ሙሳቪ ይገኙበታል፡፡

ሌላኛዋ የ27 ዓመቷ ፋጥሜ አብዱላሂ የአጎቷ ልጅና ባሏ የሆነውን በመግደል ወንጀል በምስራቅ ኢራን ኒሻፑር ውስጥ በስቅላት መቀጣቷን መግለጫው አስታውቋል፡፡

የኢራን የሰብአዊ መብቶች (IHR) በዚህ ዓመት ኢራን ውስጥ ቢያንስ 223 የሞት ቅጣት ሲመዘገብ፣ በግንቦት ወር ብቻ በትንሹ 50 ሰዎች ተገድለዋል ብሏል፡፡

በሚያዝያ ወር የፋርስ አዲስ ዓመት እና የረመዳን በዓላት ማብቃቱን ተከትሎ ግድያው እየጨመረ የመጣ ሲሆን ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ስድስት ሴቶችን ጨምሮ 115 ሰዎች ተገድለዋል፡፡

ኢራን በሴቶች ላይ በተመዘገቡት የሞት ቅጣቶች መሪነቱን የያዘች ሲሆን ከእነዚህ መካከል "ብዙዎቹ የግዳጅ ወይም የአስነዋሪ ጋብቻ ሰለባ ናቸው" ሲል መግለጫው አመልከቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG