በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቻይናው ግብርና ሚኒስትር በሙስና እየተመረመሩ ነው


እኤአ መጋቢት 2024 ፍርድ ቤት የቀረቡት የቻይና እግር ኳስ ፌደሬሽን የቀድሞ ሊቀመንበርየነበሩት ቼን ሹዩን (ፎቶ ፋይል )
እኤአ መጋቢት 2024 ፍርድ ቤት የቀረቡት የቻይና እግር ኳስ ፌደሬሽን የቀድሞ ሊቀመንበርየነበሩት ቼን ሹዩን (ፎቶ ፋይል )

የቻይናው መሪ ሺ ጂፒንግ በከፍተኛ ባለሥልጣኖቻቸው ላይ የጀመሩትን ከፍተኛ የፀረ ሙስና ዘመቻ ተከትሎ፣ የሀገሪቱ የግብርና እና የገጠር ጉዳዮች ሚኒስትር ታንግ ሬንጂያን ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ዛሬ ቅዳሜ ዘግበዋል፡፡

ሚኒስትሩ "በከፍተኛ የዲሲፕሊን እና የህግ ጥሰት ተጠርጥረዋል" ሲል የመንግስት ዜና አውታር ሲሲቲቪ ዘግቧል።

ዘገባው ታንግ ፈጽመዋል ተብለው ስለተጠረጠሩባቸው ጥሰቶች ዝርዝር መረጃ አልሰጠም።

ሺ ወደ ስልጣን ከመጡበት ከአስር ዓመታት በፊት ጀምሮ ስር የሰደደውን ሙስናን ለማስወገድ የሚደረገውን ጥረት በባላይነት ተቆጣጥረውታል፡፡

ደጋፊዎቻቸው “ዘመቻው ትክክለኛና ያልተበከለ አስተዳደርን ያበረታታል” ሲሉ ተቺዎች ግን ለቻይናው መሪ የፖለቲካ ተቀናቃኞችን የሚያስወግዱበት ጉልበት ይሰጣል ይላሉ።

ከቅርብ ወራት ወዲህ በተለይም በሀገሪቱ የፋይናንስ እና የባንክ ዘርፎች ላይ በርካታ እርምጃዎች መወሰዳቸው ታይቷል።

ባለፈው ወር እኤአ ከ 2019 እስከ 2023 የቻይና ባንክ ሊቀመንበር የነበሩት ሊዩ ሊያንጅ የተጠረጠሩበትን "ጉቦ መቀበል እና በህገወጥ መንገድ ብድሮችን የመስጠት" ወንጀል መፈጸማቸውን አምነዋል፡፡

በሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናትም ላይ ምርመራዎች ሲካሄዱ መቆየታቸው በዘገባው ተመልክቷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG