ፕሬዝደንት ጆ ባይደን እና የቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ሁለት የምርጫ ዘመቻ ክርክሮችን ለማድረግ መስማማታቸው ታውቋል።
የመጀመሪያው ክርክር እአአ ሰኔ 27/2024 በሲኤንኤን ቴሌቪዥን የሚደረግ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ መስከረም 10/2024 በኤቢሲ ቴሌቪዥን እንደሚደረግ ቀን ተቆርጦለታል።
ሲኤንኤን የሚያካሂደው ክርክር አትላንታ በሚገኘው ስቱዲዮ የሚደረግ ሲሆን፣ በአዳራሹ ተመልካቾች እንደማይኖሩ ጣቢያው አስታውቋል።
ለ30 ዓመታት የፕሬዝደንታዊ እጩዎችን ክርክር በሚያካሂደው ገለልተኛ ወገን በሚዘጋጀው ክርክር ላይ ባይደን እንደማይሳተፉ ትላንት ረቡዕ አስታውቀዋል። ሦስተኛ ወገን ሳይኖር ከትረምፕ ጋራ በቀጥታ ሁለት ክርክሮችን በሚዲያ በሚዘጋጅ መድረክ ለማድረግ ባይደን ሃሳብ አቅርበው ትረምፕ ተቀብለውታል።
መድረክ / ፎረም